ኦ ፡ የድል ፡ አምላክ ፡ ነህ (O Yedel Amlak Neh) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ኦ ፡ የድል ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ኦ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
 ኦ ፡ በክብር ፡ ያለህ ፡ ኦ ፡ የጽድቅ ፡ ንጉሥ
 ኦ ፡ ታላቅ ፡ ማዳንን ፡ ኦ ፡ አርገሃልና
 ኦ ፡ ለስምህ ፡ ይሁን ፡ ኦ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና

ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ነው ፡ መንገድህ
በላይም ፡ በሰማይ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ስምህ
ስራህ ፡ ታላቅና ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ በምድር
የምይፈራህ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ ያማያከብር

ስለበደላችን ፡ በደዌ ፡ የደቀቀው
ስለሃጥያታችን ፡ መሰዋእት ፡ የሆነው
የእግዚአብሔርን ፡ ፈቃድ ፡ በእጁ ፡ ያከናወነው
ኢየሱስ ፡ ከነፍሱ ፡ ድካም ፡ ብርሃንን ፡ ያያል
ብዙዎችን ፡ አጽዶቆ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለዋል

መጽሐፉን ፡ ዘርገተህ ፡ ማኅተሞቹን ፡ ልትፈታ
ይገባሃል ፡ ኢየሱስ ፡ እል ፡ የነሳህ ፡ ጌታ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ስለረታህ
አህዛብም ፡ ሁሉ ፡ በፊትህ ፡ ይሰግዳሉ
ለስምህም ፡ ክብር ፡ ይዘምራሉ

ታላቅ ፡ ክብሩን ፡ ትቶ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያለው
ራሱን ፡ በአምላኩ ፡ ፊት ፡ ባዶ ፡ ያደረገው
እስከመስቀልም ፡ ሞት ፡ የታዘዘው
ኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ በክብር ፡ ይመጣል