ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (Nefsie Egziabhieren Barki) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
 ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
 ሃጥያትሽ ፡ ይቅር ፡ ብሏል ፡ ደዌሽንም ፡ ፈውሷል
 ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
 ነፍሴ ፡ በምላክሽ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
 ነፍሴ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
 አምላክሽ ፡ ጠርቶሻልና ፡ ስለአንቺም ፡ ይዋጋልና
 ነፍሴ ፡ ባምላክሽ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ

ከዘመናት ፡ በፊት ፡ ጌታ ፡ አስቦሻል
በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ አምላክሽ ፡ ወዶሻል
በገዛ ፡ ልጁ ፡ ደም ፡ ራሱ ፡ አቅርቦሻል
አሜን ፡ ብይ ፡ ኃጢአትሽ ፡ ተሰርዮሻል

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢ ፡ ውጊያ ፡ ቢያበዛብሽ
መንግድሽን ፡ ሊያጠብ ፡ ዙሪያሽም ፡ ቢዚሮሽ
በአምላክሽ ፡ ታመኚ ፡ ስለአንቺ ፡ ይዋጋል
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ በፊትሽ ፡ ይሄዳል

በልጁ ፡ የዋጀሽ ፡ ጌታሽ ፡ ካንቺ ፡ ጋር ፡ ነው ፡
ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክሽ ፡ እርሱ ፡ ነው
በድካሙ ፡ ያፈራሽ ፡ ጽድቅሽ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኗል
በወደድሽ ፡ በእርሱ ፡ ምህረት ፡ አግተሻል

ስለአንቺ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሁሉን ፡ ተሸክሞአል
ስራውን ፡ ጨርሶ ፡ ተፈጽመ ፡ ብሏል ፡
ተንሽ ፡ አመስግኚው ፡ ምህረትሽን ፡ ውሰጂ
ለዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ለኢየሱስ ፡ ስገጂ