From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ና ፡ ወንድሜ ፡ ና ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ና
ነይ ፡ እህቴ ፡ ነይ ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነይ
ና ፡ ወንድሜ ፡ ያሳርፍህ ፡ ሸክምህን ፡ ያወርድልህ
ሸክምህን ፡ ያውርድልህ
ነይ ፡ እህቴ ፡ ያሳርፍሽ ፡ ሸከምሽን ፡ ያውርድልሽ
የተጨነቅህ ፡ ሸክም ፡ የከበደህ
ና ፡ ኢየሱስ ፡ ያጽናናህ ፡ ያሳርፍህ
የተጠጨነቅሽ ፡ ሸክም ፡ የከበደሽ
ነይ ፡ ኢየሱስ ፡ ያጽናናሽ ፡ ያሳርፍሽ
በሃጥያት ፡ ውስጥ ፡ ያለህ ፡ የጨለመብህ
ና ፡ ኢየሱስ ፡ ያድንህ ፡ ብርሃኑን ፡ ያብራልህ
በሃጥያት ፡ ውስጥ ፡ ያለሽ ፡ የጨለመብሽ
ነይ ፡ ኢየሱስ ፡ ያድንሽ ፡ ብርሃኑን ፡ ያብራልሽ
ተስፋ ፡ የቆረጥህ ፡ ኑሮ ፡ የመረረህ
ና ፡ ኢየሱስ ፡ ያድስሽ ፡ ኑሮን ፡ ያጣፍጥልሽ
ተስፋ ፡ የቆረጥሽ ፡ ኑሮ ፡ የመረረሽ
ነይ ፡ ኢየሱስ ፡ ያድስሽ ፡ ኑሮን ፡ ያጣፍጥልሽ
ወደ ፡ ሲኦል ፡ ሳትሄድ ፡ ሳይቀድምህ ፡ ሞት
ና ፡ ኢየሱስ ፡ ይስጥህ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
ወደ ፡ ሲኦል ፡ ስትሄጅ ፡ ሳይቀድምሽ ፡ ሞት
ነይ ፡ ኢየሱስ ፡ ይስጥሽ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
|