ምሥጋና (Mesgana) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና
 ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና
 ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ለአንተ ፡ ዝማሬ
 ሙገሳ ፡ ሙገሳ ፡ ሙገሳ ፡ ለአንተ ፡ ሙገሳ

ሰማየ ፡ ሰማያት ፡ ለአግዚአብሐር ፡ ምሥጋና
በአርያምም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና
ሰራዊቱ ፡ ሁሉ ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት
ጽሀይና ፡ ጨረቃም ፡ እርሱን ፡ አመስግኑት

ክዋክብትና ፡ ብርሃን ፡ እርሱን ፡ አመስግኑት
የሰማያት ፡ በላይ ፡ ውሃም ፡ አመስግኑት
እርሱ ፡ ብሏልና ፡ ሁኑ ፡ እነርሱም
እርሱ ፡ አዞአልና ፡ ተፈጠሩም

ሃሌሉያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስግን
እግዚአብሔርን ፡ ከሰማይ ፡ አመስግኑት
እግዜአብሔርን ፡ ከምድር ፡ አመስግኑት
የእግዚአብሔርን ፡ ስሙን ፡ አመስግኑት

የምድር ፡ ነገሥታት ፡ አህዛብም ፡ ሁሉ
አለቆችና ፡ ፈራጆች ፡ ሁሉ
ጐማሶችና ፡ ቆነጃጅቶች
አመስግኑት ፡ ሽማግሌዎች ፡ ልጆች

ሥሙ ፡ ብቻውን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል ፡
ምሥጋናው ፡ በሰማይ ፡ እና ፡ በምድር ፡ ሆኗል
የሕዝቡንም ፡ ቀንድ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል
ለእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ ምሥጋና ፡ ይገባል