ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው (Gieta Lenie Yaderekew) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ጌታ ፡ ለኔ ፡ ያድረከው ፡ ልቆጥረው ፡ አልችልም ፡ ወለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው
  ኢየሱስ ፡ ስለወደድ ፡ እወድሃለሁኝ ፡ አከብረሃለሁኝ ፡ ተመስገን ፡ እያልኩኝ

ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ሳልወድህ ፡ ወድኸኝ
በምረትህ ፡ ከበህ ፡ ቤትህ ፡ አኖርከኝ
ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ እሰዋለሁ
ምህረት ፡ ቸርነትህን ፡ እናገራለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ

አልታዘዝም ፡ ስል ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ
በፍቅርህ ፡ ገመድ ፡ ወዳንተ ፡ መልሰህ
ስወድቅ ፡ አንስተኸኝ ፡ ስዝልም ፡ ደግፈህ
እዚህ ፡ አደረሰከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ልበልህ
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነህ

ለዘለዓለምም ፡ የማትተወኝ
በዘለዓለም ፡ ፍቅርህም ፡ የወደድከኝ
ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍሴ ፡ እረኛ
ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ የማትተኛ
የማትለየኝ ፡ ስነቃም ፡ ስተኛ

አትለዋውጥም ፡ ሁልጌዜ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ስምህን ፡ ለሚጠሩህ
ኢየሱስ ፡ አምባዬ ፡ ለኔ ፡ መጠጊያዬ
ዞሮ ፡ መግቢያዬ ፡ ነህ ፡ መሸሸጊያዬ
ከመከራ ፡ ሁሉ ፡ መዳኛዬ