ጌታ ፡ ኢየሱስ (Gieta Eyesus) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡
 የሰማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ
 ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡
 የፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ
 ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው
 ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው
 ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው
 ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው

ከመጀመሪያው ፡ ያለ ፡ የሁሉ ፡ መሰረት ፡ የሆነ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሥሙ ፡ እጅግ ፡ የገነነ
በእግዚአብሔር ፡ መላዕክቶች ፡ ፊት ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የከበረ
ዙፋኑ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ በቅድስናው ፡ ያማረ
በእግዚአብሔር ፡ መላዕክቶች ፡ ፊት ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የከበረ
ዙፋኑ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ በቅድስናው ፡ ያማረ

በወርቅ ፡ መቅረዞች ፡ መሃል ፡ በክብር ፡ ያሚመላለስ
ድምጹ ፡ እንደ ፡ ብዙ ፡ ውሃዎች ፡ ድምጽ ፡ እግሮቹ ፡ እንደነጠረ ፡ ናስ
ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ ታጥቋል ፡ ዓይኖቹ ፡ የእሳት ፡ ነበልባል
ከአፉ ፡ ስይፍ ፡ ይወጣል ፡ ፊቱ ፡ አንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል
ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ ታጥቋል ፡ ዓይኖቹ ፡ የእሳት ፡ ነበልባል
ከአፉ ፡ ስይፍ ፡ ይወጣል ፡ ፊቱ ፡ አንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል

መጽሐፊንፉንም ፡ ሊወሰድ ፡ መሐተሞቹን ፡ ሊፈታ ፡
የገባዋል ፡ ኢየሱስ ፡ የጌቴች ፡ ሁሉ ፡ ጌታ
ለእግዚአብሔር ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደሙ ፡ ስለዋጀ
መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአምላኩ ፡ አዘጋጀ
ለእግዚአብሔር ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደሙ ፡ ስለዋጀ
መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአምላኩ ፡ አዘጋጀ

ለወደደን ፡ በደሙ ፡ ከኃጢአታችን ፡ ላጠበን
ለአምላኩ ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ላደረገን
በክብር ፡ ለሚመጣው ፡ ኃይል ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
እሰከዘለዓለም ፡ ድረስ ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
በክብር ፡ ለሚመጣው ፡ ኃይል ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
እሰከዘለዓለም ፡ ድረስ ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን