እንደሰው ፡ አይደለም (Endesew Aydelem) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላል
 እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላላ
 እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ይችላል
 እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ይችላላል

ሃጥያትን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይቅር ፡ ይላል
ከዓመጻም ፡ እርሱ ፡ ያነጻል
ቁጣው ፡ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ነው
ምህረቱ ፡ ግን ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው
እርሱ ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል
ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ እርሱ ፡ ፈጥራል
ለእግዚአብሔር ፡ የለም ፡ የሚሳነው
ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ሁሉን ፡ ችይ ፡ ነው

በኃይሉ ፡ ብዛትና ፡ በችሎቱ
አንዳች ፡ የማይታጣው ፡ ነው ፡ ብርቱ
እግዚአብሔር ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነው
የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ ፡ ነው
አይደክምም ፡ እርሱ ፡ አይታክትም
ማስተዋሉም ፡ አይመረመርም
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፊተኛ ፡ ነው
በኋለኞችም ፡ ዘንድ ፡ የሚኖር ፡ ነው

የእስራኤል ፡ ፈጣሪ ፡ ቅዱስ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ሥልጣን ፡ አለው ፡ ይምራል ፡ ይፈረዳል ፡
ያነሳል ፡ ይሾማል ፡ ያከብራል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለእርሱ ፡ ይቻላል
እግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ይቻለዋል
ይራራል ፡ ይወዳል ፡ ይባርካል
ይጠራል ፡ ይለያል ፡ ይልካል

ከእርሱ ፡ በፊት ፡ አምላክ ፡ አልነበረም
ከእርሱ ፡ በኋላም ፡ ማንም ፡ ዓይኖርም
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የሚያድን ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
ያደርጋል ፡ በባሕር ፡ ውስጥ ፡ መንገድን ፡
በኃይለኛ ፡ ውኃ ፡ ውስጥ ፡ መተላለፊያን
ይዋጋል ፡ ይረታል ፡ ያሸንፋል
በዙፋኑ ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል