ውለታው ፡ አምላኬ (Weletaw Amlakie) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
(Alegn Bezu Mesgana)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ውለታው ፡ አምላኬ ፡ ለኔ ፡ ያደረገው
አያልቅም ፡ ባወራው ፡ ከእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ተመስገን ፡ ልበለው

በምድር ፡ ላለው ፡ ለእንዳዱ ፡ ሰው ፡ ግድ ፡ የተሰኘው
ራሱን ፡ ለዓለም ፡ ቤዛ ፡ አድርጐ ፡ እንዲሁ ፡ የሰጠው
ለጠሉትና ፡ ላልተቀበሉት ፡ ሆኖ ፡ መስቀል ፡ ላይ
የሚያደርጉትን ፡ አያውቁምና ፡ ይቀር ፡ በል ፡ አባት ፡ ሆይ
 ያለው ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው
 ምንስ ፡ ዓይነት ፡ ቋንቋ ፡ ይችላል ፡ ሊገልጸው

በምድር ፡ ካሉ ፡ ከተዋረዱ ፡ ከድሆች ፡ በላይ
ኢየሱስ ፡ ስለእኛ ፡ ቤዛ ፡ ሆነልን ፡ መጥቶ ፡ ከሰማይ
የሁላችንን ፡ በደልና ፡ ኃጢአት ፡ ተሸከመልን
እዳችንን ፡ እርሱ ፡ ከፍለ ፡ ነጻም ፡ አወጣን
 በፍፁም ፡ ልባችን ፡ ጌታን ፡ ብንወደው
 አይገባውም ፡ ወይ ፡ ለእኛ ፡ ላደረገው

መች ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ በዚህ ፡ አበቃ ፡ የኢየሱስ ፡ ፍቅር
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ወራስህ ፡ አረገን ፡ አብሮን ፡ የምኖር
የእርሱ ፡ የሆነውን ፡ አንዳችም ፡ ሳይቀር ፡ ለእኛ ፡ ሰጠው
ባርኮቱን ፡ ሁሉ ፡ ምንም ፡ ሳይሰስት ፡ ለእኛ ፡ አፈሰሰው
 ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ብኖርለት
 ይገባዋል ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዛበት

ይህንን ፡ ውለታ ፡ የዋልልን ፡ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል
በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ናፍቀን ፡ እንቀርም ፡ መጥቶ ፡ ይወስደናል
ወዳችንን ፡ በዓይናችን ፡ እናዋለን ፡
ወድቀን ፡ ከእግሩ ፡ ስር ፡ እንወድሃለን ፡ እንለዋለን ፡
ከተስፋ ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ የተባረከው ፡ ተስፋችን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ስናየው ፡ ባይናችን