መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ (Menged Alew Gieta) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
(Alegn Bezu Mesgana)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው
  መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው
  መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው
  መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው

ባሕርን ፡ የሚከፍል ፡ ንፋስን ፡ ያመጣል
ውሃውን ፡ አስወግዶ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል
ኃይለኛውንም ፡ ወንዝ ፡ እርሱ ፡ ያቆመዋል
ደርቅ ፡ መንግድ ፡ አድርጐ ፡ ማሻገር ፡ ይችላል
 ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም
 ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም

ተራራውን ፡ አዞ ፡ ይደለድለዋል
ሸለቆውን ፡ ከፍ ፡ አድርጐ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል
የእግዚአብሔር ፡ መንገድ ፡ በቀን ፡ ብቻ ፡ አይደለም
ሌሊቱም ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ጨለማ ፡ አይሆንም
 ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም
 ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም

ደመናም ፡ ባይታይ ፡ ነፍሱም ፡ ባይነፍስም
ለመጽናናት ፡ የሚሆን ፡ ምልክት ፡ ባይኖርም
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ ውሃውን ፡ ያመጣል
የሌለውን ፡ ጠርቶ ፡ ማኖር ፡ ያውቅበታል
 ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም
 ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም