አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና (Alegn Bezu Mesgana) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
(Alegn Bezu Mesgana)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡
አምላኬ ፡ ነህና

እጅህ ፡ ሰርታኛለች ፡ ተመስገን
እፍ ፡ ብለህብኝ ፡ እስትንፋስህን
ሕያው ፡ ነፍስ ፡ ያለብኝ ፡ አደረከኝ
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ አበጀኽኝ
በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ገና ፡ ሳለሁ
በአንተ ፡ በአምላኬ ፡ ተለየሁ
ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ላዳንከኝ
ለውለታህ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋን ፡ አለኝ

በመሰዋት ፡ ጻድቁን ፡ ልጅህን
ገለጽክልኝ ፡ እኔን ፡ መውደድህን
የእዳ ፡ ጽህፈቴን ፡ ደምስሰኽው
ሕይወቴን ፡ የሞላው ፡ ምሥጋናህ ፡ ነው
ህልናዬን ፡ በደምህ ፡ ቀድሰህ
መንፈስክህ ፡ ሞላኸኝ ፡ እንዳመልክህ
በቅዱሳን ፡ መሃል ፡ አቁመኸኝ
የከበረን ፡ መዝሙር ፡ አዘመርከኝ

በሥጋዬ ፡ ከከበኝ ፡ ሃጥያት
አስጣልከኝ ፡ አድርገህልኝ ፡ ምህረት
ታማኙና ፡ ኃይለኛው ፡ ክንድህ ፡
ታድጐኛልና ፡ ላመስግንህ
በራሴ ፡ ስራ ፡ እኔን ፡ እያሳፈረክ
ሽታዬን ፡ ጠረኔን ፡ እየቀይርክ
በቃልህ ፡ ሰይፍ ፡ እየቆረጥከኝ
ያለጠባስ ፡ ቁስሌን ፡ ፈወስከኝ

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋን ፡ ለአንተ ፡
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ሰሪዬ ፡ ነህና