አቤቱ ፡ ምህረትህ (Abietu Mehereteh) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
(Alegn Bezu Mesgana)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

አቤቱ ፡ ምረትህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡
 አሜን ፡ ትሁን ፡ በአንተ ፡ እንደታመንን
 አቤቱ ፡ ምረትህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን ፡
 አሜን ፡ ፡ ትሁን ፡ በአንተ ፡ እንደታመንን

ታላቅ ፡ ምህረትህ ፡ በዝቶ ፡ በኛ ፡ ላይ
ጠላታችንን ፡ አይተህ ፡ ከሰማይ
አጠፋህልን ፡ የውኃ ፡ ራት ፡ አርገህ
በአንተ ፡ ተሻገርን ፡ ክብር ፡ ለስምህ
 ፡ በቀረንም ፡ ጉዞ ፡ በመንገዳችን
 ፡ አቤቱ ፡ ምህረትህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን

የጠላት ፡ ውጊያ ፡ ሰልፉ ፡ ሲነሳብን
በጠፋን ፡ ነበር ፡ አንተ ፡ ባትደርስልን
እንቀር ፡ ነበር ፡ እኛም ፡ ተረስተን
በምህረትህ ፡ በሕይወት ፡ አለን
 ፡ ክዚህም ፡ በሃላ ፡ በዘመናችን
 ፡ አቤቱ ፡ ምህረትህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን

ማህበል ፡ ወጀቡ ፡ ሲንሳባን
በዋጠን ፡ ነብረ ፡ ባትገስጽልልን
የማህብሉ ፡ ኃይል ፡ እንዳይስጥመን
በፈራን ፡ ጊዜ ፡ እጃንን ፡ ያዝከን
 ፡ በሰጠኸን ፡ እድሜ ፡ በዘመናችን
 ፡ አቤቱ ፡ ምህረትህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን

እስክዛሬ ፡ በቤትህ ፡ አለን
ችርነትህ ፡ ምህረትህ ፡ ተከትለውን
ቆመናል ፡ አንተ ፡ ደግፈኸን
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ ተመስገንልን
 ፡ እስከመጨረሻው ፡ ፡ ፊትክን ፡ እስክናይ
 ፡ አቤቱ ፡ ምህረትህ ፡ ትሁን ፡ ብኛ ፡ ላት
 
ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ኤልሻድዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻድይ
ኤልሻዳይ ፡ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ ፡
ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ
ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ኤልሻድዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻድይ
ኤልሻዳይ ፡ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ ፡
ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ