From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ቅንነት ፡ ተገኝቶብኝ ፡ አይደል
ጌታዬ ፡ እኔን ፡ የወደደው
ግን ፡ ከምህረቱ ፡ የተነሳ
ቆሜያለሁ ፡ ስሙን ፡ ላነሳ (፪x)
ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ ሲያስታውሰው ፡ ልቤ
በህልም ፡ ይመስለኛል ፡ ያለፍኩት ፡ በሃሳቤ
መልካሙን ፡ ቀን ፡ ያየ ፡ እግዚአብሔር ፡ የረዳው
ደግሞ ፡ ከፈል ፡ ይላል ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነቱ ፡ ሰው
መልካሙን ፡ ቀን ፡ ያየ ፡ እግዚአብሔር ፡ የረዳው
ደግሞ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ይላል ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነቱ ፡ ሰው (፪x)
አጋዥ ፡ በሌለበት ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
አጋዥ ፡ ትሆናለህ ፡ ብቻውን ፡ ለተጐዳ
የሃሩሩን ፡ ሙቀት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ
ስንቱ ፡ ቀን ፡ ወጣብህ ፡ ስንቱ ፡ ተከለለ (፪x)
ትከሻህ ፡ ለእኔ ፡ ሁሉ ፡ ምቹ ፡ ነው
ከፍ ፡ በል ፡ ምለህ ፡ ቀን ፡ ወጥቶልኝ ፡ ነው (፪x)
ከቶ ፡ አልሰጋም ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ
እኖራለሁ ፡ ተደላድዬ (፪x)
እኖራለሁ ፡ ተደላድዬ (፬x)
እንደትላንትናው ፡ መስሎት
ጠላቴ ፡ ቢወጣ ፡ ፈጥኖ (፪x)
በመንገዴ ፡ አንተ ፡ ቀድመሃል
ለጥያቄው ፡ መልስ ፡ ሰጥተሃል
ጥያቄው ፡ መልስ ፡ ሰጥተሃል (፪x)
ከእንግዲህ ፡ ላልሰጋ ፡ ልቤም ፡ ላይፈራ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሆኗል ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በተከበበ ፡ ከተማ ፡ ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ አሰማ
በተከበበ ፡ ከተማ ፡ ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ አሰማ
ረዳቴ ፡ ከፍ ፡ ይበልልኝ (፬x)
በከበበው ፡ ከተማ ፡ ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ አሰማ (፪x)
ረዳትዬ ፡ ከፍ ፡ ይበልልህ (፬x)
በከበበው ፡ ከተማ ፡ ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ አሰማ (፪x)
ረዳትዬ ፡ ከፍ ፡ ይበልልህ (፬x)
|