ምን ፡ አለኝ ፡ ለአንተ (Men Alegn Leante) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

 
ምን ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ እህህህ
የምከፍለው ፡ ነገር ፡ እህህህ (፪x)
ክበር ፡ ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ክበር (፬x)
ምን ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ እህህህ
የምከፍለው ፡ ነገር ፡ እህህህ (፪x)
ክበር ፡ ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ክበር (፬x)

እንደ ፡ ማለዳ ፡ ቀን ፡ እንደ ፡ ደመና
ሰማያትን ፡ ከድኗል ፡ የአንተ ፡ ምሥጋና
እኔም ፡ ጨምራለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃሃ (፬x)

እኔስ ፡ ስለአንተ ፡ ባወራ ፡ ባወራ ፡ አሃሃሃ
ተዓምራቶችህ ፡ በየተራ ፡ አሃሃ
እንኳን ፡ ቆጥሬ ፡ ልዘልቀው (፪x)
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ አልችለው
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ አልችለው (፪x)

አድነከኛል ፡ እና ፡ አከብርሃለሁ (፪x)
ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፬x)
አድነከኛል ፡ እና ፡ አከብርሃለሁ (፪x)
ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፬x)

ኧረ ፡ እኔስ ፡ እንዴት ፡ ልበል ዝም (፪x) ፡ አልቻልኩም
ላመስግንህ ፡ አምላኬ ፡ ዘወትር
ምህረትህን ፡ እያሰብኩ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከውን
ለእኔስ ፡ እጅግ ፡ በዛ ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x)
ምሥጋናን ፡ ልሰዋ ፡ ለረዳኸኝ ፡ ጌታ (፪x)
ለእኔስ ፡ እጅግ ፡ በዛ ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x)
ምሥጋናን ፡ ልሰዋ ፡ ለረዳኸኝ ፡ ጌታ (፪x)