ጉበኛ ፡ ነኝ (Gubegna Negn) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

የተስፋውን ፡ ቃል ፡ ከሩቅ ፡ አይተው ፡ እንደተሳለሙት
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ጊዜ ፡ ተሰጠኝ ፡ እድል ፡ የማየት
ሁሉን ፡ ወራሽ ፡ ባደረገው ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ተናገረኝ
ቅባቴን ፡ ለክብር ፡ አድርጐታል ፡ ምሳሌውን ፡ ልፈልግ (፪x)

በማየው ፡ ነገር ፡ አልረካም ፡ አዲስን ፡ ነገር ፡ ስፈልግ
በራሴ ፡ ዘመን ፡ አካሄዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አድርጌ ፡ ልለፍ
(፪x)

ጉበና ፡ ነኝ ፡ በቅጥር ፡ ላይ ፡ ልቆም ፡ ተነሳሁ
አስጨናቂውን ፡ በጭንቅ ፡ ላስለቅቀው (፪x)

ታማኝ ፡ አድርገህ ፡ የቆጠርከኝ
የቤትህ ፡ አገልጋል ፡ እንድሆን ፡ ሾምከኝ
የልብህን ፡ ሃሳብ ፡ በእኔ ፡ ለመፈጸም
የእኔ ፡ ሁኔታ ፡ አንተን ፡ አላገደም (፪x)

ታዲያ ፡ ዘመኔን ፡ ለአንተ ፡ ብያለሁ
እንድትገዛም ፡ እኔ ፡ ፈቅጃለሁ (፪x)

በእኔ ፡ ላይ ፡ ጉዳይ ፡ አለህ
ስትጠራኝ ፡ አላማ ፡ አለህ
ክብርህን/ልጅህን ፡ ልትገልጽ ፡ በእኔ
ወደሃል ፡ ጌታ ፡ በዘመኔ (፪x)

ለአላማዬ ፡ ጨካኝ ፡ እርስቴን ፡ የማልሸጥ
ጥፋትን ፡ በመጸየፍ ፡ በጽድቅ ፡ እየኖርኩኝ
ተነሳሁ ፡ ፊትለፊት ፡ ጠላቴን ፡ ልገጥመው
የወሰደውን ፡ ላስመልስ ፡ ምርኮን ፡ ልበዝብዘው
ተነሳሁ ፡ ፊትለፊት ፡ ጠላቴን ፡ ልገጥመው
የወሰደውን ፡ ላስመልስ ፡ ምርኮን ፡ ልበዝብዘው (፪x)

የኪዳን ፡ ሰው ፡ ተናጣቂ ፡ ጦረኛ ፡ ነው
ለበራለት ፡ እውነት ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ የማይል ፡ ነው
ለዓለም ፡ ክብር ፡ ተመሳስሎ ፡ ዐይኖርም
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ያለውን ፡ ፀጋ ፡ አይስደፍርም (፪x)

የጠላቴን ፡ እጅ ፡ ዘርግቻለው ፡ ላልመልሰው
ድል ፡ የራሴ ፡ ነው ፡ እጄም ፡ ይረታል
ነገር ፡ ልፈላልገው (፪x)

ለትውልድ ፡ ተሟጋች ፡ እኔ ፡ እያለሁ
አይሰራም ፡ ከእጄ ፡ አያመልጥ ፡ ጠላቴ
የናፈቀውን ፡ አይወርስም (፫x)
አይወርስም ፡ አይወርስም