በውኃ ፡ ላይ ፡ ሄደ (Beweha Lay Hiede) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

 
አዲስ ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ እኔን ፡ ለማስለመድ
ደግሞ ፡ አደረገ ፡ በውኃ ፡ ላይ ፡ መንገድ (፪x)

አዝ፦ በውኃ ፡ ላይ ፡ ሄዶ ፡ አሳይቶኛል (፪x)
ታዲያ ፡ እኔ ፡ እንዳልሄድ ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል (፪x)
በውኃ ላይ ፡ መሄድ ፡ እሱ ፡ ከቻለ (፪x)
እራሱን ፡ ተማምኖ ፡ አንችሂን ፡ ነይ ፡ ካለ ፡ አንተን ፡ ና ፡ ካለ (፪x)
አልፈራም ፡ እኔም ፡ አልፈራም (፮x)

እኔ ፡ ያየሁት ፡ ውሃውን ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ የማይሆን ፡ የለም
በውኃ ፡ ላይ ፡ መሄድ ፡ አልችልም ፡ እያሉ
እኔስ ፡ ስራመድ ፡ አይተው ፡ ጉድ ፡ አሉ (፪x)

አዝ፦ በውኃ ፡ ላይ ፡ ሄዶ ፡ አሳይቶኛል (፪x)
ታዲያ ፡ እኔ ፡ እንዳልሄድ ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል (፪x)
በውኃ ላይ ፡ መሄድ ፡ እሱ ፡ ከቻለ (፪x)
እራሱን ፡ ተማምኖ ፡ አንችሂን ፡ ነይ ፡ ካለ ፡ አንተን ፡ ና ፡ ካለ (፪x)
አልፈራም ፡ እኔም ፡ አልፈራም (፮x)

ውሃውም ፡ ያው ፡ ነዉ ፡ ባሕሩም ፡ ያው ፡ ነዉ
እኔ ፡ ግን ፡ የያዝኩት ፡ የአምላኬን ፡ ቃል ፡ ነዉ (፫x)

እርሱ ፡ ነይ ፡ ካለ ፡ መሄድ ፡ የእኔ ፡ ነው (፪x)
ግራ ፡ ቀኝ ፡ አይቶ ፡ መፍራት ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)
እርሱ ፡ ና ፡ ካለ ፡ መሄድ ፡ የእኔ ፡ ነው (፪x)
ግራ ፡ ቀኝ ፡ አይቶ ፡ መፍራት ፡ ምንድን ፡ ነው
መፍራት ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ረገጥ ፡ አደረኩኝ ፡ ማዕበሉን ፡ በድፍረት
ለካስ ፡ ድምጽ ፡ ብቻ ፡ ነበረ ፡ ወይ ፡ ጩኸት (፬x)

. (1) .