በስራህ (Beserah) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በስራህ ፡ ሁሌ ፡ ትክክል ፡ ቃልህን ፡ ስትናገር ፡ እውነት
በልቡ ፡ እንደአንተ ፡ ትሁት
እንደአንተ ፡ አላየሁም ፡ የሚነገርለት
እንደአንተ ፡ አልሰማሁም ፡ የሚባልለት
እንደአንተ ፡ አላየሁም ፡ የሚነገርለት
እንደአንተ ፡ አልሰማሁም ፡ የሚባልለት (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ የሚመስልህ ፡ የለህም (፬x)

ተሳስተሃላል ፡ አስተካክል ፡ ማን ፡ ይልሃል
አንድም ፡ ቀን ፡ በስራህ ፡ ማን ፡ አምቶሃል (፪x)
ማንም ፡ ተሟግቶ ፡ አንተን ፡ አይረታም
የመማለጃ ፡ ብዛት ፡ ፈቀቅ ፡ አያደርግህም (፪x)
እውነተኛ ፡ እንደአንተ ፡ ማነው
ሁልጊዜ ፡ ትክክል ፡ ኧረ ፡ እንዳንተ
(፪x)

እንዳንተ ፡ አላየሁም ፡ የሚነገርለት
እንዳንተ ፡ አልሰማሁም ፡ የሚባልለት
እንዳንተ ፡ አላየሁም ፡ የሚነገርለት
እንዳንተ ፡ አልሰማሁም ፡ የሚባልለት (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ የሚመስልህ ፡ የለህም (፬x)

ስምህን ፡ ላከብር ፡ ፊተኛ ፡ ሆኛለሁ
በመንገዶችህ ፡ ንጹህ ፡ እንደአንተ ፡ አላየሁ
በመንገዶችህ ፡ ንጹህ ፡ እንደአንተ ፡ አላየሁ (፪x)
ኧረ ፡ አምላኬ ፡ ንጉሤ ፡ አጣሁልህ
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ ጌታዬ ፡ ተማርኮብህ (፪x)

አምላኬ ፡ ሰፊ ፡ ነህ ፡ ከአእምሮዪ ፡ በላይ
እኔ ፡ አልገምትህ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ (፪x)
ከምልህ ፡ በላይ ፡ በላይ (፬x)
ለዘለዓለም ፡ ብሩክ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፬x)
ለዘለዓለም ፡ ብሩክ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፬x)