በሰማይ (Besemay) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): ፮:0፩
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ በፍፁም ፡ የለም ፡ አንተን ፡ የሚመስል (፪x)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ በፍፁም ፡ የለም ፡ አንተን ፡ የሚመስል (፪x)

በደመናትም ፡ ላይ ፡ ይራመዳል
ፍጥረታትንም ፡ ሁሉ ፡ እርሱ ፡ ያዛል
ጥንቃቄ ፡ የተሞላ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ የለም ፡ እርሱን ፡ የሚረታ
ጥንቃቄ ፡ የተሞላ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ የለም ፡ እርሱን ፡ የሚረታ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ በፍፁም ፡ የለም ፡ አንተን ፡ የሚመስል (፪x)

ለዓለምና ፡ ለዘላለም
ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ የምንለው
መጀመሪያ ፡ መጨረሻ ፡ የለው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስራውን ፡ ያድንቀው
መጀመሪያ ፡ መጨረሻ ፡ የለው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስራውን ፡ ያድንቀው (፪x)

ስራህን ፡ ደግሞ ፡ ጥበብህን
ዝናህን ፡ ከሩቅ ፡ ሰማሁ
ስቀርብህ ፡ ከሰማሁት ፡ በላይ
ሆነህ ፡ አገኘሁህ (፪x)

ሁሉን ፡ አልፌ ፡ እሄዳለሁ
የሚቃወመኝ ፡ ከቶ ፡ ማነው
ሁሉን ፡ ሰብሬ ፡ እሄዳለሁ
ሰባሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

አልፎ ፡ ሄዷል ፡ ከበሩ
አልፌ ፡ እሄዳለሁ
ንጉሡን ፡ ተከትዬ
መቼ ፡ አፍራለሁ (፭x)

አልፎ ፡ ሄዷል ፡ ከበሩ
አልፌ ፡ እሄዳለሁ
ንጉሡን ፡ ተከትዬ
መቼ ፡ አፍራለሁ (፭x)

እግዚአብሔርን ፡ የታመኑ ፡ ዓይናቸውን ፡ ያድሳሉ
እንደንስር ፡ በከፍታ ፡ ላይያዙ ፡ ይወጣሉ (፪x)

ይሄን ፡ . (1) .
በምንም ፡ ነገር ፡ ላይደርስብኝ
አስጥሎኛል ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፯x)