በማደሪያህ (Bemaderiyah) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Nazareth Amanuel Shebsheba Choir 5.jpg


(5)

ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
(Tsehay Atetelqem Keto Benie Lay)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በማደሪያህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተቀምጠህ ፡ የለ ፡ ወይ (፪x)
አንተ ፡ እያለህ ፡ የእኔ ፡ አባት
እንዴት ፡ ይገባል ፡ ልቤ ፡ ስጋት (፪x)

በመንገዴ ፡ ቅጥርን ፡ ቀጥሮ
አታልፈውም ፡ ይህን ፡ ከቶ
ብሎ ፡ ያለው ፡ ያ ፡ ተራራ
ስፍራን ፡ ለቋል ፡ ስምህን ፡ ስጠራ (፪x)

አንተ ፡ እያለህ ፡ የእኔ ፡ አባት
እንዴት ፡ ይገባል ፡ ልቤ ፡ ሥጋት (፪x)

ሰማይ ፡ የአንተ ፡ ዙፋንህ
ምድር ፡ የአግርህ ፡ መርገጫ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላስተያይህ
አንተ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x)
እኩያ ፡ አይገኝለህም (፲፪x)

አንዱ ፡ ለአንዱ ፡ ቅድስናህን ፡ ሲያወሩ
በምሥጋናቸው ፡ ማደሪያህን ፡ የሞሉ
(፪x)
እኔ ፡ ስላለኝ ፡ ምሥጋና ፤ ይዤ ፡ ተነሳሁኝና
ዙፋንህ ፡ ስር ፡ መጣሁኝ ፡ ልሰዋ ፤ ዛሬም ፡ እንደገና

ቢወጣልኝ ፡ ኖሮ ፡ እንዲህ ፡ አመስግኜ (፪x)
በሰጠሁህ ፡ ነበር ፡ አንድ ፡ ቃል ፡ ጠቅልዬ (፪x)
ግን ፡ እንደው ፡ ስራህን ፡ ስላየሁ ፡ በዐይኔ
ተመስገን ፡ ስልህ ፡ ባሰብኝ ፡ እኔ
(፪x)

የቱ ፡ ተቀንሶ ፡ የቱ ፡ ይጨመራል (፪x)
አንተ ፡ ያረክልኝ ፡ ስንቱ ፡ ይቆጠራል (፪x)
ዛሬም ፡ ተነሳሁ ፡ ልዘምር (፪x)
በክብር ፡ ላይ ፡ ክብር ፡ ልጨምር (፬x)

ክብርህን ፡ ማውራት ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ ይላል (፪x)
ስራህን ፡ ብናገር ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ ይላል (፪x)
ክብርህን ፡ ማውራት ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ ይላል (፪x)
ስራህን ፡ ብናገር ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ ይላል (፪x)

ኦሆ ፡ ቢዘመርልህ ፡ ኦሆ ፤ ኧረ ፡ አንተ ፡ ሲያንስህ
ኦሆ ፡ ቢሰገድልህም ፡ ኦሆ ፤ ኧረ ፡ አንተ ፡ ሲያንስህ (፪x)
ኦሆ (፬x)