ተራራውን ፡ ስትንድ ፡ ሸለቆውን ፡ ስትሞላ (Terarawen Setened Sheleqowen Setmola) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አዝ፦ ተራራውን ፡ ስትንድ ፣ ኦሆሆ
ሸለቆው ፡ ሲሞላ ፣ አሃሃ (፪x)
ማነው ፡ ያልገመተው ፡ መኖርህን
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አሃሃ (፪x)

ልቤ ፡ አረፈብህ (፪x)
ሥምንም ፡ አገኘሁ ፡ በአንተ ፡ በዳንኩብህ (፪x)

ከታናሹ ፡ ጋር ፡ ከፍ ፡ ባለው ፡ ሥፍራ ፡ ላይ ፡ ትቀመጣለህ
ምሥጋናን ፡ ከእርሱ ፡ አንተ ፡ ትወስዳለህ (፪x)
የምሥጋናዬ ፡ መልካሙ ፡ መዓዛ
አንተን ፡ ያክብርህ ፣ መቅደስህን ፡ ይሙላ (፫x)

ከታናሹ ፡ ጋር ፡ ከፍ ፡ ባለው ፡ ሥፍራ ፡ ላይ ፡ ትቀመጣለህ
ምሥጋናን ፡ ከእርሱ ፡ አንተ ፡ ትወስዳለህ (፪x)
የምሥጋናዬ ፡ መልካሙ ፡ መዓዛ
አንተን ፡ ያክብርህ ፣ መቅደስህን ፡ ይሙላ (፫x)

አሁንማ ፡ የእኔ ፡ የምለው ፡ አለኝ
አሁንማ ፡ ወደ ፡ እልፍኙ ፡ ገባሁ
አሁንማ ፡ እታመነዋለሁ
አሁንማ ፡ የልቤን ፡ አገኘሁ (፪x)

አዝ፦ ተራራውን ፡ ስትንድ ፣ ኦሆሆ
ሸለቆው ፡ ሲሞላ ፣ አሃሃ (፪x)
ማነው ፡ ያልገመተው ፡ መኖርህን
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አሃሃ (፪x)

ልቤ ፡ አረፈብህ (፪x)
ሥምንም ፡ አገኘሁ ፡ በአንተ ፡ በዳንኩብህ (፪x)

የምድር ፡ ፍጥረት ፡ አንዱ ፡ ባንዳቸው ፡ ይደነቃሉ
ዓይኖቼ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ ያያሉ (፬x)

የምድር ፡ ፍጥረት ፡ አንዱ ፡ ባንዳቸው ፡ ይደነቃሉ
ዓይኖቼ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ ያያሉ (፬x)

በራልኝ (፫x)
እኔም ፡ አየሁኝ (፪x)

በብርሃንህ ፡ ብርሃንን ፡ አየሁ (፪x)
ከጨለማ ፡ ውስጥ ፡ እኔ ፡ አምልጫለሁ
እኔ ፡ አምልጫለሁ (፪x)

ታላቅ ፡ ሁን ፡ ዛሬም ፡ ታላቅ ፡ ሁን
ታላቅ ፡ ሁን ፡ ሁሌም ፡ ታላቅ ፡ ሁን (፪x)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሥራህም ፡ ታላቅ (፬x)

ታላቅ ፡ ሁን ፡ ዛሬም ፡ ታላቅ ፡ ሁን
ታላቅ ፡ ሁን ፡ ሁሌም ፡ ታላቅ ፡ ሁን (፪x)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሥራህም ፡ ታላቅ (፬x)