ትላንት ፡ አንተ ፡ ነበርክ ፡ ያለህ (Telant Ante Neberk Yaleh) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አዝ፦ ትናንት ፡ አንተ ፡ ነበርክ ፡ ያለኸኝ
ዛሬም ፡ አንድ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ (፪x)

የልቤንም ፡ ሁሉ ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ጠቅልዬ
ተባረክ ፡ እላለሁ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ ብዬ
ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ ብዬ (፪x)

ሌላማ ፡ ለአንተ ፡ ምንስ ፡ ይባላል
ከልብ ፡ ከሆነ ፡ ይሄ ፡ ይበቃሃል
ይሄ ፡ ይበቃሃል (፪x)

ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ ለእኔ ፡ ሆነኸኛል
ገና ፡ ከልጅነቴ ፡ ጠብቀህ ፡ አሳድገኸኛል
ከሗላ ፡ ከፊቴ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቅጥር ፡ ቀጥረሃል
ጠላቴ ፡ ከአንተ ፡ አልፎ ፡ መች ፡ እኔን ፡ ይነካኛል (፪x)

አዝ፦ ትናንት ፡ አንተ ፡ ነበርክ ፡ ያለኸኝ
ዛሬም ፡ አንድ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ (፪x)

የልቤንም ፡ ሁሉ ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ጠቅልዬ
ተባረክ ፡ እላለሁ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ ብዬ
ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ ብዬ (፪x)

ሌላማ ፡ ለአንተ ፡ ምንስ ፡ ይባላል
ከልብ ፡ ከሆነ ፡ ይሄ ፡ ይበቃሃል
ይሄ ፡ ይበቃሃል (፪x)

አንተ ፡ ያልከው ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ ሆነ
ከሆነው ፡ ሁሉ ፡ የለ ፡ ያልሆነ
(፪x)
ምድርን ፡ እንኳን ፡ ፈጥሯል ፡ ቃልህ
ማን ፡ በአንተ ፡ ሰጠው ፡ ሊጠረጥርህ
ምድርን ፡ እንኳን ፡ ፈጥሯል ፡ ቃልህ
ማን ፡ በአንተ ፡ ሰጠው ፡ ሊጠረጥርህ (፪x)

ባሕርን ፡ ከፍሎ ፡ ሕዝቡን ፡ መራ
ተባለልህ ፡ ትላንት ፡ ድንቅ ፡ ሥራ
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ይባስ ፡ ብለህ
አቀረብኸኝ ፡ ወደ ፡ ራስህ ፡ እርቅን ፡ ፈጥረህ
(፪x)

ባሕርን ፡ ከፍሎ ፡ ሕዝቡን ፡ መራ
ተባለልህ ፡ ትላንት ፡ ድንቅ ፡ ሥራ
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ይባስ ፡ ብለህ
አቀረብኸኝ ፡ ወደ ፡ ራስህ ፡ እርቅን ፡ ፈጥረህ
(፪x)

ኧረ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ምህረትህ ፡ በዛልኝ (፬x)

ኧረ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ምህረትህ ፡ በዛልኝ (፬x)