From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
{ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ይናገራል ፣ አዎ ፡ ይናገራል
[አንደበቴ ፡ ክብርህን ፡ ያወራል] (፬x)} (፪x)
{ ክብርህ ፡ ከሰማያት ፡ ከፍታ ፡ በላይ ፡ ነው
ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ ፡ ነው
ምሥጋናህ ፡ በምድር ፡ ሞልቶ ፡ ተትረፍርፎአል
እንዳንተ ፡ ገናና ፡ ኧረ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ አል?] (፪x)
[ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና] (፬x) } (፪x)
{ ሰማያት ፡ የእጆችህን ፡ ሥራ ፡ ተናገሩ ፡ ቢባል
ስለአንተ ፡ መተረክ ፡ ቢችሉ ፡ ስንቱን ፡ ባወሩ
እኔ ፡ ግን ፡ ተአምራቶችህን ፡ እናገራለሁ
ፈቅጄ ፡ ምሥጋናን ፡ ከልቤ ፡ እሰጥሃለሁ} (፪x)
{ አንተን ፡ የምባርክበት ፡ መንፈስህን ፡ ሰጥተኸኛል
ችዬ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ? ፡ ፍቅርህ ፡ ሁሌ፡ ያዘምረኛል} (፪x)
{ ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ይናገራል ፣ አዎ ፡ ይናገራል
[ አንደበቴ ፡ ክብርህን ፡ ያወራል] (፬x) } (፪x)
{ የከፍተኛነቴ ፡ ሰይፍ ፡ የረድኤቴ ፡ ጋሻ ፡ ነህ
[ በሕያዋን ፡ ምድር ፡ እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ] (፬x) } (፪x)
{ ልኡል ፡ የሰውን ፡ ፍርድ ፡ ትመልስ ፡ ዘንድ
[ ታማኝ ፡ ነህ ፡ እህህህ] (፬x) } (፪x)
{ የእኔ ፡ ፍርድ ፡ ይጣመም ፡ ዘንድ
[ አንተ ፡ እሺ ፡ አትልም ] (፬x) } (፪x)
{ [ ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ ከትውልድ ፡ ጅማሬ] (፪x)
[ ፍርድህ ፡ አልተዛባም ፡ ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ ] (፪x) } (፪x)
አቤት ፡ ሲያምርብህ ፡ ጌታዬ ፡ ስትሠራ
አቤት ፡ ሲያምርብህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ስትሠራ
አቤት ፡ ሲያምርብህ ፡ ጌታዬ ፡ ስትሠራ
አቤት ፡ ሲያምርብህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ስትሠራ
|