ምህረትህ (Mehereteh) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ምህረትህን ፡ ትውልድ ፡ ይናገራል
ልቤስ ፡ ቢሆን ፡ ኧረ ፡ መች ፡ ረስቶሃል
ያደረግኸው ፡ አልቀረ ፡ እንደ ፡ ዋዛ
ልዝረፍልህ ፡ ቅኔን ፡ እያበዛሁ (፪x)

አንተኑ ፡ ብዬ ፡ ላምልክህ ፡ አላማዬ
ከደጅህ ፡ መጣሁ ፡ ምሥጋናን ፡ ተሸክሜ (፪x)

ምን ፡ አሃሃሃ ፡ ሃሃ ፡ እልሃለሁ
እንከን ፡ አይወጣው ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
አንዳች ፡ ሳላወራ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሳልለው
ሥራህ ፡ ምስክር ፡ ነው (፪x)
 
ሕያው ፡ ነህ፡ ለዘለዓለም (፪x) ሕያው
ሕያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ሕያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም

እንደ ፡ አንተ ፡ አላየሁም ፡ በፍቅርህ ፡ ብዛት
ሁሉንም ፡ የሚወድ ፡ አይነካካው ፡ ወረት
ይገርማል
በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሥምህ ፡ ይጠራ
አቻ ፡ የለህም ፡ ሆነህ ፡ ገናና (፪x)

እንዳንተ፡ አላየሁም ፡ በፍቅርህ ፡ ብዛት
ሁሉንም ፡ የሚወድ ፡ አይነካካው ፡ ወረት
ይገርማል

በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሥምህ ፡ ይጠራ
አቻ ፡ የለህም ፡ ሆነህ ፡ ገናና (፪x)

በምን ፡ አንደበት ፡ እንዴት ፡ ይወራ
የትኛው ፡ ቀርቶ ፡ የቱ ፡ ይጠራ
ሥራህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የመድሃኒቴ
በልቤ ፡ አምላክ ፡ ጸና ፡ ጉልበቴ (፪x)

ልቤ ፡ ጸና (፬x)