ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል (Madanu Kemaebelu Fetnual) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

መርከቤ ፡ ከውሃው ፡ በላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
መጨነቅ ፡ ከእንግዲህ ፡ አብቅቷል (፪x)
 
እያለ ፡ ጌታ ፡ መርከቡ ፡ ላይ
የምን ፡ ሥጋት ፡ ነው ፡ ወጀብ ፡ ቢታይ
እያለ ፡ ጐኔ ፡ የሚያኮራ
በጣር ፡ ሰዓትም ፡ የሚጠራ (፪x)

የፈጠነ ፡ ቢመስል ፡ ወጀብ ፡ ማእበሉ
ነፋሳት ፡ በአንድ ፡ ላይ ፡ ተባብረው ፡ ቢያይሉ
ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ ሰው ፡ ምድር ፡ ብትረዳቸው
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የበላያቸው (፪x)

አልፈራም ፡ እኔ ፡ አልፈራም (፮x)

እያለ ፡ ጌታ ፡ መርከቡ ፡ ላይ
የምን ፡ ሥጋት ፡ ነው ፡ ወጀብ ፡ ቢታይ
እያለ ፡ ጐኔ ፡ የሚያኮራ
በጣር ፡ ሰዓትም ፡ የሚጠራ (፪x)

(ከግቤ ፡ እደርሳለሁ) ፡ ከግቤ ፡ እደርሳለሁ
ከባሕሩ ፡ ዳርቻ
(እንቁዬን ፡ አልጥልም) ፡ እንቁዬን ፡ አልጥልም
አይደለሁ ፡ ለብቻ (፬x)

(ያሰጠመኝ ፡ መስሎት) ፡ ያሰጠመኝ ፡ መስሎት
ማእበሉ ፡ ሲያፏጭ
(እኔ ፡ ግን ፡ አመለጥኩ) ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አመለጥኩ
ጠላቴን ፡ በአቋራጭ (፬x)

(መርከቤ) ፡ መርከቤ ፡ ከውሃው ፡ በላይ
(ከፍ ፡ ከፍ) ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል
(ማዳኑ) ፡ ማዳኑ ፡ ከማእበሉ ፡ ፈጥኗል
(መጨነቅ) ፡ መጨነቅ ፡ ከእንግዲህ ፡ አብቅቷል (፪x)

(እያለ ፡ ጌታ) ፡ እያለ ፡ ጌታ
(መርከቡ ፡ ላይ) ፡ መርከቡ ፡ ላይ
(የምን ፡ ሥጋት ፡ ነው) ፡ የምን ፡ ሥጋት ፡ ነው
(ወጀብ ፡ ቢታይ) ፡ ወጀብ ፡ ቢታይ
(እያለ ፡ ጐኔ) ፡ እያለ ፡ ጐኔ ፡ የሚያኮራ
(በጣር ፡ ሰዓት) ፡ በጣር ፡ ሰዓት
(የሚጠራ) ፡ የሚጠራ (፪x)

አልፈራም ፡ እኔ ፡ አልፈራም (፴፪x)