ለአላማህ ፡ አገኘኸኝ (Lealamah Agegnehegn) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በዓላማ ፡ አገኘኸኝ
ለሃሳብህ ፡ ለየኸኝ
ደነቀኝ ፡ የአንተ ፡ ምርጫ
ጥሪህን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አጸናህ (፪x)

እንዳስለመድኸኝ ፡ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ማመሥገን
በልቤ ፡ ሞልቷል ፡ ለማድነቅ ፡ አንተን (፪x)

አንተን ፡ ለማድነቅ ፡ አንተን (፪x)

አንተ ፡ የልጅነት ፡ የልቤ ፡ ወዳጄ
ፍቅርህን ፡ አስባለሁ ፡ ጐህ ፡ ሲቀድ ፡ ማልጄ
ተነሽ ፡ ቢለኝ ፡ ነቃሁ ፡ ይሄ ፡ ትዝታዬ
ውለታህን ፡ አስቆጠረኝ ፡ ላመሥግን ፡ በተራዬ
ተነስ ፡ ቢለኝ ፡ ነቃሁ ፡ ይሄ ፡ ትዝታዬ
ውለታህን ፡ አስቆጠረኝ ፡ ላመሥግን ፡ በተራዬ (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ መልካም ፡ በማድረጉ
ደስ ፡ ይለዋል ፡ ለእኔ ፡ ለልጁ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ አልተገኘልህም (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሉያ ፣ ሉያ ፣ ሉያ (፬x)

የእጆችህ ፡ ሥራ ፡ ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ነው
በእውነትና ፡ በቅን ፡ የተሠራ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ምሥጋናን ፡ ብጨምር ፡ ባበዛ
ሳነሳሳ ፡ ብውል ፡ ሥራህን ፡ ባወራ (፪x)

ብዙ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ነው
ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

የሚያስገርም ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ሰማሁ
ውበትህ ፡ ስላስደመመኝ ፡ ይህን ፡ ውዴን ፡ አየሁ (፪x)

ለካስ ፡ የእራሴ ፡ ወዳጅ ፡ ነው
ምድርን ፡ ያስደነቀው
አስገራሚው ፡ የእራሴ ፡ ጌታ ፡ ነው
ምድርን ፡ ጉድ ፡ ያሰኘው (፪x)

ጉድ ፡ ያሰኘው
ምድርን ፡ ጉድ ፡ ያሰኘው