በከፍታ ፡ ከፍ ፡ አድርጌ (Bekefeta Kef Adregie Akebrehalehu) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በከፍታ ፡ ከፍ ፡ አድርጌ ፡ አከብርሃለሁ
በሕይወቴ ፡ ገዢ ፡ አድርጌ ፡ እሾምሃለሁ (፪x)

አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ሥምህ ፡ ለእኔ ፡ ጋሻ ፡ ነው
ልብህ ፡ መታመኛዬ
ክንድህ ፡ ታዳጊዬ ፡ ነው (፪x)

ክንድህ ፡ ታዳጊዬ ፡ ነው (፬x)

አምላኬ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ግሩም
ሥምህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም
አላማህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም
የሚሆንህ ፡ አቻ ፡ የለም (፪x)

አንተ ፡ በዘለዓለም ፡ ተራሮች ፡ ላይ
ውበትህ ፡ እንደ ፡ ንጋት ፡ የሚታይ
ፍጥረትን ፡ አማልሎ ፡ አስከተለ
አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው (፪x)

የሚወራ ፡ የሚወራ
እጅ ፡ በአፍ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ሥራ
(፪x)
ትውልድ ፡ ይናገር ፡ ዛሬም ፡ ይናገር
ያየ ፡ የሰማ ፡ ዝናህን ፡ ይመስክር
እጅ ፡ በአፍ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ሥራ
ልቤ ፡ ሸፈተ ፡ ክብርህን ፡ ሲያወራ (፪x)

ስወጣም ፡ አልሰጋ ፡ ስገባም ፡ አልሰጋ
ብርቱ ፡ አማኑኤል ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ከፊቴ ፡ ቀድመህ ፡ ትወጣለህ
ጠላቶቼን ፡ ትመታለህ (፪x)

ብዙ ፡ ኃይልህ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የተገለጠው
አንዳች ፡ ኃይል ፡ የለም ፡ የሚቋቋመው
የጠላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ይሄዳል
ይገሰግሳል ፡ ማን ፡ ያቆመዋል
ኦ ፡ ማን ፡ ያቆመዋል (፫x)

ብዙ ፡ ኃይልህ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የተገለጠው
አንዳች ፡ ኃይል ፡ የለም ፡ የሚቋቋመው
የጠላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ይሄዳል
ይገሰግሳል ፡ ማን ፡ ያቆመዋል
ኦ ፡ ማን ፡ ያቆመዋል (፫x)

ስወጣም ፡ አልሰጋ ፡ ስገባም ፡ አልሰጋ
ብርቱ ፡ አማኑኤል ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ከፊቴ ፡ ቀድመህ ፡ ትወጣለህ
ጠላቶቼን ፡ ትመታለህ (፬x)