በገናናው ፡ ዙፋንህ (Begenanaw Zufaneh) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 7:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ከገናናው ፡ ዙፋንህ
ክብር ፡ በሞላበት ፡ መቅደስህ
አይሃለሁ ፡ ተውበሃል
ክብር ፡ ይሁንልህ ፡ በማደሪያህ (፪x)

በሰማያት ፡ ያለኸው ፡ በላይ
ናፍቆቴ ፡ የልቤ ፡ ርሃብ
ከሞት ፡ ወጥመድ ፡ ያመለጥኩብህ
ወግ ፡ ማዕረግ ፡ የቀመስኩብህ (፪x)

አንድ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አንድ
ብርቅ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አንድ
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ የእኔ ፡ መደምደሚያ
አንተ ፡ ካለህበት ፡ ይድረስ ፡ ከማደሪያ
ከቅዱስ ፡ ማደሪያ ፡ አሃ (፪x)

ክብርህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ
ውበትህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ
ጥበብህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ
ሥራህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ
አንተ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ
ሥምህ ፡ ገነነ ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)

ቅድስና ፡ እና ፡ እውነት ፡ በመቅደስህ (፪x)
ክብር ፡ ታላቅነት ፡ የራስህ (፮x)
ቅድስና ፡ እና ፡ እውነት ፡ በመቅደስህ (፪x)
ክብር ፡ ታላቅነት ፡ የራስህ (፲x)

ከአእላፍ ፡ ይልቅ ፡ በአደባባዮች ፡ ያለች
አንዲቷ ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ትሻላለች (፬x)
ከአእላፍ ፡ ይልቅ ፡ በአደባባዮች ፡ ያለች
አንዲቷ ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ትሻላለች (፬x)

ጌታዬ ፡ ነገሬን ፡ እስኪጨርስ ፡ ድረስ ፡ አያርፍም (፬x)
ያመንኩትን ፡ አውቃለሁኝ ፡ እና ፡ አላፍርም (፬x)

እኔ ፡ ስለ ፡ እርሱ ፡ ሳወራ
ሰርቷል ፡ ጌታ ፡ የእኔን ፡ ሥራ (፪x)

እኔ ፡ ስለ ፡ እርሱ ፡ ስናገር
ሰራው ፡ ጌታ ፡ የእኔን ፡ ነገር (፪x)

(ያመንኩትን) ፡ ያመንኩትን
(አውቃለሁና) ፡ አውቃለሁና
(አላፍርም) ፡ አላፍርም (፬x)