ባሕሩ ፡ ተከፍሎ ፡ ባላይ ፡ እንኳን (Baheru Tekeflo Balay Enkuan) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(4)

ማዳኑ ፡ ከማዕበሉ ፡ ፈጥኗል
(Madanu Kemaebelu Fetnual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ባሕሩ ፡ ተከፍሎ ፡ ባላይ ፡ እንኳን
እኔ ፡ ግን ፡ ከበሮዬን ፡ አነሳለሁ (፪x)
ሁኔታው ፡ ባይመችም ፡ እንኳን
እኔ ፡ ግን ፡ ለሥምህ ፡ እዘምራለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ ለሥምህ ፡ እዘምራለሁ (፪x)

በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰነው ፡ ሥፍራ
የሕግ ፡ መምህር ፡ በዚያ ፡ በረከትን (፫x) ፡ አዟል
በዚያ ፡ በረከትን (፫x) ፡ አዟል

በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰነው ፡ ሥፍራ
የሕግ ፡ መምህር ፡ በዚያ ፡ በረከትን (፫x) ፡ አዟል
በዚያ ፡ በረከትን (፫x) ፡ አዟል

ጌታ ፡ የእኔ ፡ ከፍታ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ (፪x)

እኔ ፡ ከቀስት ፡ ፊት ፡ ፈጥኜ ፡ አመልጥ ፡ ዘንድ
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ምልክት ፡ አደረግህ
ሥምህን ፡ ለሚፈሩ ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ትላለህ
ሁሌም ፡ ከቀን ፡ በላይ ፡ ቀን ፡ ትጨምራለህ (፪x)

በጠላቴ ፡ ፊት ፡ እኔን ፡ አክብረህ
እንዲህ ፡ አምሮብኝ ፡ ታኖረኛለህ (፪x)

ጌታ ፡ የእኔ ፡ ከፍታ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ (፪x)

ሞቴን ፡ የተመኘ ፡ በእኔ ፡ ፋንታ ፡ ገብቷል
ውርደቴን ፡ (ጌታ ፡ ለውጠሃል) ፡ ጌታ ፡ ለውጠሃል (፪x)

አቤቱ ፡ በኃይልህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በማዳንህ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፪x)

(በበጐ ፡ በረከት) ፡ በበጐ ፡ በረከት ፡ ደርሰህልኛል (፬x)

(በቃሉ) ፡ በቃሉ ፡ የታመነ ፡ ያለውን ፡ የሚያደርግ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ቢፈለግ (፪x)

(የለም) ፡ የለም ፡ የለም ፡ የለም ፡ አዎ ፡ የለም
የለም ፡ የለም ፡ (ቢፈለግም) ፡ ቢፈለግም ፡ የለም (፪x)

ክብርንና ፡ ግርማን ፡ ለብሰህ (፫x)
ብርሃንን ፡ እንደ ፡ ልብስ ፡ ለብሰህ
አንተ ፡ ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ (፬x)

ክብርንና ፡ ግርማን ፡ ለብሰህ (፫x)
ብርሃንን ፡ እንደ ፡ ልብስ ፡ ለብሰህ
አንተ ፡ ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ (፬x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይስተካከላል
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ ከፍ ፡ ብለሃል (፪x)

ጌታ ፡ የእኔ ፡ ከፍታ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ (፮x)