የመማፀኛ ፡ ከተማዬ (Yemematsegna Ketemayie) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አዝ፦ ኃጢአትን ፡ ሰርቼ ፡ ሊገድሉኝ ፡ ሲያሳድዱኝ
በመማፀኛ ፡ ከተማ ፡ ውስጥ ፡ ዘልዬ ፡ ገባሁኝ
የመማፀኛ ፡ ከተማዬ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በእርሱ ፡ ተሸሽጋ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ (፪x)

ሰለሞን ፡ የሰራው ፡ መቅደስ ፡ ፈረሰ
የኢያሪኮም ፡ ግንብ ፡ በጩኸት ፡ ወደቀ
የእኔ ፡ ግን ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ተናውጦም ፡ አያውቅም
አይወድቅም ፡ ኢየሱስ ፡ አይነቃነቅም

አዝ፦ ኃጢአትን ፡ ሰርቼ ፡ ሊገድሉኝ ፡ ሲያሳድዱኝ
በመማፀኛ ፡ ከተማ ፡ ውስጥ ፡ ዘልዬ ፡ ገባሁኝ
የመማፀኛ ፡ ከተማዬ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በእርሱ ፡ ተሸሽጋ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ

የሙሴ ፡ መሸሸጊያ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ነው
የእኔ ፡ ግን ፡ ማምለጫ ፡ ሰማያዊ ፡ ነው
የያዕቆብ ፡ መሸሸጊያው ፡ የላባ ፡ ቤት ፡ ቀረ
የእኔ ፡ ግን ፡ ማምለጫ ፡ ኢየሱስ ፡ በሰማይ ፡ ከበረ

አዝ፦ ኃጢአትን ፡ ሰርቼ ፡ ሊገድሉኝ ፡ ሲያሳድዱኝ
በመማፀኛ ፡ ከተማ ፡ ውስጥ ፡ ዘልዬ ፡ ገባሁኝ
የመማፀኛ ፡ ከተማዬ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በእርሱ ፡ ተሸሽጋ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ

መኖሪያዬ ፡ የእኔ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ነው
ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ የፀና ፡ ግንብ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ እኔ ፡ ምንም ፡ አልሆን
መሸሸጊያዬ ፡ ሆኗል ፡ በመከራ ፡ ቀን

አዝ፦ ኃጢአትን ፡ ሰርቼ ፡ ሊገድሉኝ ፡ ሲያሳድዱኝ
በመማፀኛ ፡ ከተማ ፡ ውስጥ ፡ ዘልዬ ፡ ገባሁኝ
የመማፀኛ ፡ ከተማዬ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በእርሱ ፡ ተሸሽጋ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ (፪x)