የለህም ፡ እኩያ (Yelehem Ekuya) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ክቡር (፫x) ፡ ነህ ፡ ክቡር ፡ ነህ
ኃያል (፫x) ፡ ነህ ፡ ኃያል ፡ ነህ
ቅዱስ (፫x) ፡ ነህ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
አባት ፡ አንተን ፡ ላምልክህ (፪x)
ላምልክህ ፡ ኦ ፡ ላምልክህ (፪x)

አምላክ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ንጉሥ ፡ ነህን ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ዝቅ ፡ ብለን ፡ እንሰግድልሃለን
ደስ ፡ እያለን ፡ እናመልክሃለን
አምላክ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)

ሰባቱን ፡ ማኅተም ፡ በእጆቹ ፡ የያዘ ፡ የፍጥረታት ፡ ጌታ
እንተ ፡ ግን ፡ ችለሃል ፡ ሁሉን ፡ ልትረታ
ማህተሙን ፡ ልትፈታ
ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ ያመሰግኑሃል ፡ ያሞጋግሱሃል
ከእግሮችህ ፡ ሥር ፡ ሆነው ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ይሉሃል
ክብርን ፡ ይሰጡሃል

አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ንጉሥ
ነህና ፡ ኢየሱስ (፪x)

አምላክ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ንጉሥ ፡ ነህን ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ዝቅ ፡ ብለን ፡ እንሰግድልሃለን
ደስ ፡ እያለን ፡ እናመልክሃለን
አምላክ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ የዘለዓለም ፡ አንተ (፪x)

በምሥጋና ፡ የተፈራ ፡ በቅድስና ፡ የከበርክ
በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ለብሰህ
በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የተቀመጥክ
ሰማይና ፡ ምድር ፡ የአንተን ፡ ክብር ፡ አወሩ
ፍጥረታትም ፡ ደስ ፡ አላቸው ፡ ለሥምህ ፡ ዘመሩ (፪x)

ኦ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የለህ ፡ እኩያ
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፪x)

ከፍ ፡ ባለ ፡ ረጅም ፡ ዙፍን ፡ ላይ
እጅግ ፡ ባማረ ፡ መንበር ፡ ላይ
ተቀምጦ ፡ ያለ ፡ በሰማይ
እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ኤልሻዳይ (፪x)

ኤልሻዳዩ ፡ እግዚአብሔር) (፪x) ፡ ዛሬም ፡ ክበር
ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ዛሬም ፡ ንገሥ
እንተ ፡ ለዘላለም ፡ ሕያው ፡ ነህ (፪x) በክብር ፡ ያለህ
እንተ ፡ ለዘላለም ፡ ሕያው ፡ ነህ (፪x) በክብር ፡ ያለህ

የአብርሃም ፡ የይስሃቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ
ዛሬም ፡ ተመለክ ፡ ዛሬም ፡ ተወደስ (፬x)