From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ የሕይወት ፡ ሽታ
እናከብረዋለን ፡ ነፍሳችን ፡ ነቅታ (፪x)
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው (፪x)
በላይ ፡ በሰማይ ፡ ለከበረው
እንደ ፡ በግ ፡ ለእኔ ፡ የታረደው
የናሱን ፡ ደጆች ፡ ለሰባበረው
ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ውዳሴ ፡ ይድረሰው
አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ የሕይወት ፡ ሽታ
እናከብረዋለን ፡ ነፍሳችን ፡ ነቅታ (፪x)
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው (፪x)
ቆጥሬ ፡ የማልዘልቀው ፡ ውለታ ፡ አለብኝ
ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ የዋለልኝ
ምላሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ በብዙ ፡ ጥቂት
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ወዳጄ ፡ ላለኸው ፡ በሰማይ
አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ የሕይወት ፡ ሽታ
እናከብረዋለን ፡ ነፍሳችን ፡ ነቅታ (፪x)
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው (፪x)
ውበቱ ፡ የሚያምር ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ ውዴ
ግርማው ፡ የሚያስፈራ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ንጉሤ
ነገሥታት ፡ ኃያላን ፡ አለቆች ፡ በሙሉ
ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ እያሉ ፡ ለሥሙ ፡ ይገዛሉ
አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ የሕይወት ፡ ሽታ
እናከብረዋለን ፡ ነፍሳችን ፡ ነቅታ (፪x)
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው
ውዳችን ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ክበር ፡ ክበር ፡ እንበለው
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ እንበለው (፪x)
|