ሥመ ፡ ገናና (Seme Genana) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ዜማ ፡ ደግሞ ፡ በዝማሬ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ዛሬ
ሰማይ ፡ ሰማያትም ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ ይስጡ
ምድርም ፡ ዕልል ፡ ትበል ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ
ምሥጋናውን ፡ አምጡ ፡ ለእርሱ ፡ ለንጉሡ
ለንጉሡ ፡ ምሥጋና ፡ እናቅርብ ፡ እንደገና (፪x)

ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛ
እርሱን ፡ እናድንቀው ፡ ይክበር ፡ በምሥጋና
በዘመናት ፡ ውስጥ ፡ ሁሉን ፡ የቻለ
ጌትን ፡ የሚተካ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ

በክብር ፡ ላይ ፡ ክብር ፡ ክብርን ፡ ደርበህ
ደግሞም ፡ በሰማያት ፡ ከፍ ፡ ብለህ
በሚያስፈራ ፡ ግርማ ፡ ብርሃንን ፡ ለብሰህ
አንተ ፡ ትኖራለህ ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ትኖራለህ ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስ ፡ ትኖራለህ ፡ ለዘለዓለም

ከአባቶቻችን ፡ ጋር ፡ ቀድሞ ፡ የነበረው
የነአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው
ክንዱ ፡ አይዝል ፡ አይደክም ፡ ከቶ ፡ አይታክተው
እርሱ ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ማነው ፡ የሚችለው
ከአምልክቶች ፡ ሁሉ ፡ ክንዱ ፡ የበረታ ፡ ነው
ብርቱ ፡ ነው ፡ የበረታ ፡ አክብሩት ፡ በዕልልታ (፪x)

አማኑኤል (፫x) ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል
ኤሎሂ (፫x) ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
እግዚአብሔር (፫x) ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር (፪x)

ውዴ ፡ አቤት ፡ ግርማህ ፡ አስፈሪ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የክብርህ ፡ ፀዳል ፡ ያበራል
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ያማረ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ ገናና ፡ ነው

ሥመ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና
ሥመ ፡ ገናና
ገናና ፡ ታላቅ ፡ ነህና (፫x)