ነፍሴ ፡ ሆይ (Nefsie Hoy) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አዝነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም ፡ የተቀደሰ ፡ ሥሙን
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ምሥጋናውንም ፡ አትርሺ

ኃጢአትሽን ፡ ሁሉ ፡ ይቅር ፡ ያለሽ
በደልሽንም ፡ ሁሉ ፡ ያላሰበ
ሕይወትሽን ፡ ከክፍት ፡ ያዳነ
በምህረቱ ፡ በቸርነቱ ፡ የከለለ

ማነው (፬x)
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x)

አዝነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም ፡ የተቀደሰ ፡ ሥሙን
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ምሥጋናውንም ፡ አትርሺ

ነፍሴ ፡ ያዳነሽ ፡ ውቡ ፡ አበባ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ
በደም ፡ ተጨማልቀሽ ፡ ከሩቅ ፡ ያየሽ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ የወደደሽ
እርሱ ፡ ነው ፡ የሳሮን ፡ አበባ (፪x)

አዝነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
አጥንቶቼም ፡ የተቀደሰ ፡ ሥሙን
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ምሥጋናውንም ፡ አትርሺ

ብርሃንም ፡ ሆኖ ፡ ብርሃንን ፡ አሳየሽ
ጨለማሽን ፡ ገፎ ፡ ሕይወትን ፡ አደለሽ
እግዚአብሔር ፡ በክብር ፡ በኢየሱሱ ፡ ሰወረሽ
የመንግሥቱ ፡ ዜጋ ፡ ዜጋዊ ፡ አረገሽ
ነፍሴ ፡ ምን ፡ ትያለሽ ፡ ኧረ ፡ ይህን ፡ ጌታ (፬x)

አዝነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (፬x)
ሃሌሉያ
አጥንቶቼም ፡ የተቀደሰ ፡ ሥሙን
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ምሥጋናውንም ፡ አትርሺ