ምሥጋና ፡ ይወዳል (Mesgana Yewedal) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ምሥጋና ፡ ለጌታ ፡ ይድረስ ፡ እንደገና
ዝማሬ ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ እንደጋና
በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና
ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ እንደገና (፪x)

ምሥጋናን ፡ ይወዳል ፡ እርሱ
አምልኮን ፡ ይወዳል ፡ እርሱ
ዝማሬን ፡ ይወዳል ፡ እርሱ
ዕልልታን ፡ ይወዳል ፡ እርሱ
ክብርን ፡ እንስጠው ፡ ለንጉሡ (፪x)

ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ አምልኮ
ስግደትም ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ጌታ
ስግደትም ፡ ለአንተ ፡ ነው
ስግደትም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)

ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ይገባሃል ፡ ውዴ
ይገባሃለ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆንክ ፡ ንጉሤ (፪x)

በበጉ ፡ ዙፋንን ፡ ፊት ፡ ሆነን ፡ በደስታ (፪x)
ክብርን ፡ እንሰጣለን ፡ ይክበርልን ፡ ጌታ (፪x)
ከማደሪያው ፡ ይድረስ ፡ ይግባ ፡ ምሥጋናችን (፪x)
ዕልልታ ፡ ያውደው ፡ ይድመቅ ፡ አምላካችን
ይድመቅ ፡ አምላካችን (፪x)

እስቲ ፡ ዕልል ፡ ዕልል ፡ በሉለት (፪x)
እናሸብሽብ ፡ እንስገድለት
እናሸብሽብ ፡ እንስገድለት (፪x)

ማንም ፡ በማይቀርበው ፡ ብርሃን ፡ ተከበሃል
ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይቀርብሃል (፪x)
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ ፀዳል ፡ ያበራል
ጨለማ ፡ መቼ ፡ ፊትህ ፡ ይቆማል
ጨለማ ፡ መቼ ፡ ፊትህ ፡ ይቆማል (፪x)

አቻም ፡ የሌለህ ፡ አምላክ ፡ ነህ
እኔ ፡ እሰግዳለሁ ፡ ለክብርህ
በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኛለሁ
ለአምላኬ ፡ ለአንተ ፡ አሸበሽባለሁ
እሰግዳለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ለንጉሡ
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በመቅደሱ
እቀኛለሁ ፡ ለኢየሱስ ፡ ለንጉሡ
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በመቅደሱ (፪x)

ኦሆ ፡ ክብር ፡ ይድረስህ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)

እስቲ ፡ ዕልል ፡ ዕልል ፡ በሉለት (፪x)
እናሸብሽብ ፡ እንስገድለት
እናሸብሽብ ፡ እንስገድለት (፪x)

ኦሆ ፡ ክብር ፡ ይድረስህ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)