ጉልበት ፡ ሆንከን (Gulbet Honken) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

የመንፈሱ ፡ ኃይል ፡ እረድቶናል
መሸሸጊያ ፡ ዋሻ ፡ ሆኖልኛል
ጠላታችንን ፡ አዋርዷል
ከክበር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ አሻግሮናል

አዝ፦ እናመስግንሃለን ፡ ጉልበት ፡ ሆንከን
እናከብርሃለን ፡ ብርታት ፡ ሆንከን
ጌታ/ኢየሱስ ፡ ተመስገን (፪x)

ጨለማችን ፡ ይኸው ፡ በአንተ ፡ በራ
እስራታችንም ፡ ተፈታ
ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር
ወደር ፡ አቻ ፡ የለህም

አዝ፦ እናመስግንሃለን ፡ ጉልበት ፡ ሆንከን
እናከብርሃለን ፡ ብርታት ፡ ሆንከን
ጌታ/ኢየሱስ ፡ ተመስገን (፪x)

በመከራችን ፡ ረድኤት ፡ ሆንከን
በክንድህም ፡ ብርታት ፡ እዚህ ፡ አደረስከን
ለክብርህም ፡ ቆመን ፡ እንዘምራለን
ታላቅነትህን ፡ እናውጃለን

አገነነው ፡ ለእኔስ ፡ ምህረቱን (፬x)
በዝቶልኛል ፡ ለእኔስ ፡ ቸርነቱ (፬x)

ያኔ ፡ ምን ፡ እመስል ፡ ነበር
በኃጢአት ፡ ገመድ ፡ ታስሬ
ኢየሱስ ፡ ስትመጣ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ እኔ
ከላዬ ፡ ወደቀ ፡ ቀንበሬ (፪x)

ምን ፡ ልበል ፡ ዛሬ (፪x)
ክበር (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ውዴ
ንገሥ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ውዴ

አገነነው ፡ ለእኔስ ፡ ምህረቱን (፬x)