እሰይ ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር ፡ ክበር (Esey Eyesus Keber Keber) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አዝአቤት (፬x) በታላቅ ፡ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ፡ ከበረ
ፍጥረታት ፡ ተገዙለት ፡ ኃያላን ፡ ሰገዱለት
ምሥጋና ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
ከፍ ፡ አለ ፡ እጅግ ፡ በሰማይ

እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የክብር ፡ ዘውድ: የጫነው
አቤት ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የድል ፡ አክሊል ፡ የጫነው

በሰማያት ፡ በታላቅነት ፡ በደመናት ፡ ላይ ፡ የሚሄደው
በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ለብሶ ፡ ብርሃን ፡ የተጐናፀፈው
የተፈራ ፡ የተከበረ ፡ በውበቱ ፡ እጅግ ፡ ያማረ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ በዙፋኑ ፡ ፀንቶ ፡ ያለ

እናመስግነው (፫x)
ኢየሱስ ፡ የለም ፡ መመስለው (፪x)

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው (፪x)

እግዚአብሔር (፪x) ፡ ዘላለም ፡ የምትኖር
ኢየሱስ (፪x) ፡ ሥምህ ፡ የሚፈውስ (፪x)

አዝአቤት (፬x) በታላቅ ፡ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ፡ ከበረ
ፍጥረታት ፡ ተገዙለት ፡ ኃያላን ፡ ሰገዱለት
ምሥጋና ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
ከፍ ፡ አለ ፡ እጅግ ፡ በሰማይ

እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የክብር ፡ ሰውን ፡ የቻለው
አቤት ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የድል ፡ አክሊል ፡ የጫነው

በተቀደሰው ፡ ቅዱስ ፡ መቅደስ
በግርማ ፡ ሞገስ ፡ የሚመላለስ
እርሱ ፡ ነውና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
ዘላለም ፡ ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ በነፍሴ

ክቡር ፡ ነውና (፫x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ሥመ ፡ ገናና
ንጉሥ ፡ ነውና (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ የጀግኖች ፡ ጀግና

አዝአቤት (፬x) በታላቅ ፡ ሞገስ
እሰይ (፬x) ኢየሱስ ፡ ከበረ
ፍጥረታት ፡ ተገዙለት ፡ ኃያላን ፡ ሰገዱለት
ምሥጋና ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
ከፍ ፡ አለ ፡ እጅግ ፡ በሰማይ

እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የክብር ፡ ሰውን ፡ የቻለው
አቤት ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ነው (፪x)
የድል ፡ አክሊል ፡ የጫነው

በሰማያት ፡ ሰማይ ፡ ያለ
ጥንትም ፡ በፊትም ፡ የነበረ
በዘመናት ፡ የሸመገለ
እግሩ ፡ እንደ ፡ ነሃስ ፡ የጋለ
ድምፁ ፡ ነጐድጓድ ፡ የሚያስፈራ
ብቻውን ፡ ድንቅ ፡ የሚሰራ
ደማቅ ፡ ብርሃን ፡ የተሞላ
እንደ ፡ ቀትር ፡ የሚያበራ

ኦ ፡ ኦሆሆሆ (፫x)
ብርሃን ፡ ይወጣል ፡ ከፊቱ
የክበር ፡ ፀዳል ፡ ነው ፡ ውበቱ (፬x)