ብርሃን ፡ ወጣልኝ (Berhan Wetalegn) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ከፍ ፡ በል ፡ በማደሪያ ፡ ላይ ፡ እግዚአብሔር
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ እግዚአብሔር
በመቅደስህ ፡ ውስጥ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርክልህ (፪x)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
ምላስም ፡ በፍጥረት ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ይበልህ
ፅድቅህን ፡ ያውራልህ

ልዑል ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ (፬x)
ማደሪያህን ፡ ይሙላ
ምሥጋናዬ ፡ አንተን ፡ ያክብርህ ፡ ጌታዬ
ክብርህን ፡ ይሙላው ፡ ዕልልታዬ (፪x) ፡ ሃሌሉያ
ክብር ፡ ለሆነው ፡ ገናና
እሰዋለሁኝ ፡ ምሥጋና (፪x) ፡ ሃሌሉያ

ምሥጋና (፪x) ፡ ለጌታ ፡ እንደገና
ዝማሬ (፪x) ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ዛሬ (፪x)

ያደረገልኝ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዕልልታዬ ፡ መቅደሱን ፡ ልሙላው (፪x)

ውለታው ፡ ያለባችሁ ፡ አመስግኑት
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብላችሁ ፡ ስገዱለት
ፍቅሩም ፡ የበዛላችሁ ፡ አሸብሽቡ
በምሥጋናም ፡ ማደሪያው ፡ ግቡ (፪x)

ምሥጋና (፪x) ፡ እላለሁ
ዝማሬ (፪x) ፡ እላለሁ
ዕልልታ ፡ ዕልልም ፡ እላለሁ
እኔ ፡ ከሞት ፡ ድኛለሁ (፪x)

መድኃኒቴ ፡ ለእኔስ ፡ እጅጉን ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)
ከሲዖልም ፡ መሃል ፡ አንተ ፡ ታወጣለህ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ሆነኝ ፡ ጨለማዬ ፡ በራ (፪x)
ብርሃን ፡ ወጣልኝ ፡ ስሆን ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
ስሆን ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ (፪x)

ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሆኖኛል (፬x)

እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ሆነኝ ፡ ጨለማዬ ፡ በራ (፪x)
ብርሃን ፡ ወጣልኝ ፡ ስሆን ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
ስሆን ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ (፪x)

የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ አንተ ፡ ነህ
በምክርህ ፡ ልቤን ፡ ታሳርፋለህ
በምክርህ ፡ ልቤን ፡ ታሳርፋለህ (፪x)

ሸለቆ ፡ ባይሞላ ፡ እኔ ፡ አላማርርም
በአምላኬ ፡ ላይ ፡ አፌን ፡ በከንቱ ፡ አልከፍትም
ከሁሉም ፡ ይበልጣል ፡ እንተን ፡ ማመስገን
ታላቅ ፡ ነህ ፡ እያሉ ፡ ክብርህን ፡ ማግነን
ታላቅ ፡ ነህ ፡ እያሉ ፡ ክብርህን ፡ ማግነን (፪x)

ክብርህ ፡ እንደ ፡ ደመና ፡ ሰማያትን ፡ ሸፍኗል
ኦሆ ፡ ሰማያትን ፡ ሸፍኗል
ምሥጋና ፡ ለዘለዓለም ፡ ለሥምህ ፡ ይገባሃል
ኦሆ ፡ ይገባሃል ፡ ኦሆ (፫x)

ክብርህ ፡ እንደ ፡ ደመና ፡ ሰማያትን ፡ ሸፍኗል
ኦሆ ፡ ሰማያትን ፡ ሸፍኗል
ምሥጋና ፡ ለዘለዓለም ፡ ለሥምህ ፡ ይገባሃል
ኦሆ ፡ ይገባሃል ፡ ኦሆ (፯x)