አምላኬ ፡ ይወደኛል (Amlakie Yewedegnal) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

አምላኬ ፡ ይወደኛል ፡ እኔም ፡ እወደዋለሁ
ፍቅሩን ፡ ቸርነቱን ፡ በዘመኔ ፡ ቀምሻለሁ
በጊዜው ፡ አይቻለሁ ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ ሲሰራ
በሽተኛን ፡ ስትፈውስ ፡ ዓይነ ፡ ስውር ፡ ስታበራ (፪x)

አዝ፦ ዎሆሆሆ
ለዘለዓለም ፡ ክብር
ለዘላለም ፡ ንገሥ (፪x)

እንባዬ ፡ ታብሶልኝ ፡ ከማደሪያው ፡ ገብቻለሁ
ሳልፈልገው ፡ ፈልጐ ፡ በእጆቹ ፡ ደርሻለሁ
ለወደደኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ
እሰግዳለሁ ፡ ተንበርክሬ (፪x)

አዝ፦ ዎሆሆሆ
ለዘለዓለም ፡ ክብር
ለዘላለም ፡ ንገሥ (፪x)

ጉልበትም ፡ ሆንህልኝ ፡ ጠላቴንም ፡ እረገጥኩት
ስለዚህም ፡ ወደድኩህ ፡ ክበር ፡ ክበርም ፡ አልኩህ
ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ
ለዘለዓለም ፡ ምትኖር ፡ ነግሥህ (፪x)

አዝ፦ ዎሆሆሆ
ለዘለዓለም ፡ ክብር
ለዘላለም ፡ ንገሥ (፪x)

ተመሥገን ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃይሌን ፡ አደስክልኝ
በኮረብታም ፡ አቆምከኝ ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበርልኝ
ውዴ ፡ ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል
ክበር ፡ ክበር ፡ ያሰኘኛል (፪x)

ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ባለሞገስ ፡ ባለዝና
እንዳልናወጥ ፡ እግሮቸን ፡ አፀና ፡ ምሥግና (፪x)

በፀጋው ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ምሥግና
በክብሩ ፡ ወንበር ፡ ፊት ፡ ምሥግና
እሰዋለሁ ፡ ለሆነው ፡ ገናና (፪x)

ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ባለሞገስ ፡ ባለዝና
እንዳልናወጥ ፡ እግሮቸን ፡ አፀና ፡ ምሥግና (፪x)