አልቆጥብም ፡ ድምጼን (Alqotebem Demtsien) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን
(Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

Lyrics.jpg


(1)

ብርሃን ፡ ወጣልኝ
(Berhan Wetalegn)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Nazareth Amanuel Shebsheba Choir)

ዕልል ፡ እላለሁ ፡ በመቅደሱ
ክብርን ፡ እሰጣለሁ ፡ ለንጉሡ
ዝቅም ፡ እላለሁ ፡ በዙፋኑ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ሁሌ ፡ እዘምራለሁ
ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ሁሌ ፡ እዘምራለሁ
ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ (፪x)

ምሥጋናዬ ፡ በፊቱ ፡ ይብዛና
አምልኮዬ ፡ በፊቱ ፡ ይብዛና
ሽብሸባዬ ፡ በፊቱ ፡ ይብዛና
ይክበርልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደገና (፪x)

ሁሉም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ማድረግ ፡ አይሳነው
በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሮ
በቤቱ ፡ ያኖረኛል ፡ ይኸው ፡ አሳምሮ
በቤቱ ፡ ያኖረኛል ፡ ይኸው ፡ አሳምሮ (፪x)

የኃያላንን ፡ ቀስት ፡ ተሰብራለህ
ለደካማው ፡ ኃይልን ፡ ታስታጥቃለህ
ምስኪኑን ፡ ከመሬት ፡ ታነሳለህ
ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣዋለህ (፪x)

ይህ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ
ይድረስ ፡ ለእርሱ ፡ መስዕዋቴ (፪x)

አትታበዩ ፡ በኩራት ፡ አትናገሩ
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ አውሩ
የሞትን ፡ አውጅ ፡ እርሱ ፡ ይሽራል
ባማረ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ያስቀምጣል
ባማረ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ያስቀምጣል (፪x)