From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
አባ. ናትናኤል ፡ ታየ (Abba. Natnael Taye)
|
|
()
|
ማን ፡ ብዬ ፡ ልጥራ ፡ ስምህን (Man Beyie Letra Semehen)
|
ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአባ. ናትናኤል ፡ ታየ ፡ አልበሞች (Albums by Abba. Natnael Taye)
|
|
ኀጢአት ፡ መሆኑን ፡ እየተረዳን ፡ በደምብ ፡ አውቀነው
የምንአለበት ፡ ተዉ ፡ ባክህን ፡ ብለን ፡ አለፍነው
በስግ ፡ ስሜት ፡ እየተነዳን ፡ ስንሸፋፍነው
ያወቅነው ፡ መስሎን ፡ እንዲያው ፡ በመላ ፡ የዘመኑ ፡ ሰው
በሰንበት ፡ ብቻ ፡ ስንንመላለስ ፡ ልማድ ፡ ሆኖብን
አይፈሪሳዊ ፡ እያለ ፡ ጌታ ፡ ግብዞች ፡ ሲለን
እንደ ፡ መቃብር ፡ ከላይ ፡ ስንታይ ፡ ኖራ ፡ ተቀብተን
ቅሚያና ፡ ዝርፊያ ፡ ውስጣችን ፡ ሞልቷል ፡ በመንፈስ ፡ ላየን
አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው
ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ትንኝ ፡ አጥርተው ፡ ግመል ፡ እየዋጡ ፡ ቢመላለርሱ
የበግ ፡ ለምድ ፡ ለብሰው ፡ ለታይታ ፡ ብቻ ፡ ጻድቅ ፡ ቢመስሉም
ጌታ ፡ ይመጣል ፡ በእጁ ፡ መርሽ ፡ ይዞ ፡ ቤቱን ፡ ሊያጠራ
ዝም ፡ ብሎ ፡ አያይም ፡ በመቅደሱ ፡ ውስጥ ፡ ኀጢአት ፡ ሲደራ
ስንዴና ፡ እንክርዳድ ፡ ጐተራ ፡ አይገባም ፡ ብደምብ ፡ ሳይጠራ
ከመንጋው ፡ መሃል ፡ ቢመሳሰሉ ፡ ሆኖ ፡ በጋራ
ጌታ ፡ ሳይለው ፡ ይህ ፡ ክርስቲያን ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቢለው
መጋፋት ፡ አይደል ፡ የእርሱ ፡ መለኪያው ፡ ጌታን ፡ መኖር ፡ ነው
አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው
ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ምንም ፡ ቢማሩ ፡ ለውጥ ፡ ከሌለ ፡ መምህር ፡ ቢባሉ
አያስደንቅም ፡ ወረቀት ፡ ይዘው ፡ ዲግሪ ፡ ቢጭኑ
አንቱ ፡ ቢባሉ ፡ ለምን ፡ ይጠቅማል ፡ ሕይወት ፡ ከሌለው
ዝናና ፡ ክብር ፡ በምድር ፡ ያለው ፡ ሁሉም ፡ ጠፊ ፡ ነው
እንዲያው ፡ በጭፍር ፡ ምንም ፡ ሳይገባው ፡ የጌታ ፡ አላማው
ቢሰብክ ፡ ቢዘምር ፡ ቃሉን ፡ አጣፍጦ ፡ ወደድኩህ ፡ ቢለው
ለራሱ ፡ ክብር ፡ እያመቻቸ ፡ የኖረውን ፡ ሰው
ተጠቀመብኝ ፡ አለ ፡ እንጂ ፡ እራሱ ፡ ጌታ ፡ መች ፡ አለ
አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው
ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
|