ይመለካል ፡ ገና (Yemelekal Gena) - አባ. ናትናኤል ፡ ታየ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አባ. ናትናኤል ፡ ታየ
(Abba. Natnael Taye)

Lyrics.jpg


()

ማን ፡ ብዬ ፡ ልጥራ ፡ ስምህን
(Man Beyie Letra Semehen)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአባ. ናትናኤል ፡ ታየ ፡ አልበሞች
(Albums by Abba. Natnael Taye)

 
አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ዝማሬ ፡ ለጌታ ፡ ምስጋና
ገና ፡ እዘምራለሁ ፡ ገና ፡ እንደገና (፪x)
ገና ፡ እንደገና (እንደገና) (፰x)

ለመጀመሪያማ ፡ ሁሉም ፡ ይንቀዋል
እየዋለ ፡ ሲያድር ፡ ጉዱ ፡ ይገለጣል
የናቀው ፡ ተንቆ ፡ ከእግሩ ፡ ስር ፡ ሲወድቅ
ጌታ ፡ እንደዚህ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ሲያንበረክክ

እንዲህ ፡ አልነበርኩኝም ፡ እኔ (፫)
ለውጦኝ ፡ አየሁ ፡ መድህኔ (፪)
አምላኬ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ
አያልቅም ፡ ቢወራ ፡ ሁሌ (፭x)

ገና ፡ መች ፡ ተጀመረና
ይነገራል ፡ ይሰበካል ፡ ገና
ጌታ ፡ የኔ ፡ ገናና
ገና ፡ ይመለካል ፡ ገና
(፪x)
ይመለካል ፡ ገና ፣ ይመለካል ፡ ገና (፬x)

አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ዝማሬ ፡ ለጌታ ፡ ምስጋና
ገና ፡ እዘምራለሁ ፡ ገና ፡ እንደገና (፪x)
ገና ፡ እንደገና (እንደገና) (፰x)

ውዳሴና ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ላውራ
በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ህይወቴን ፡ ለሰራ
ለጨነቀው ፡ ደራሽ ፡ ልዩ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ለዚህ ፡ ለኢየሱሴ ፡ ይድረሰው ፡ ምስጋና

እንዲህ ፡ አልነበርኩኝም ፡ እኔ (፫)
ለውጦኝ ፡ አየሁ ፡ መድህኔ (፪)
አምላኬ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ
አያልቅም ፡ ቢወራ ፡ ሁሌ (፭x)

ገና ፡ መች ፡ ተጀመረና
ይነገራል ፡ ይሰበካል ፡ ገና
ጌታ ፡ የኔ ፡ ገናና
ገና ፡ ይመለካል ፡ ገና
(፪x)
ይመለካል ፡ ገና ፣ ይመለካል ፡ ገና (፬x)