ወዳጅ ፡ ማን ፡ አለ (Wedaj Man Ale) - ናሆም ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናሆም ፡ ማርቆስ
(Nahom Markos)


(1)

እውነተኛ ፡ ሰላም
(Ewnetegna Selam)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናሆም ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Nahom Markos)

የማይከዳ ፡ ትቶ ፡ የማይሄድ
ሃብት ፡ ንብረት ፡ ፊት ፡ አይቶ ፡ የማይወድ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማን ፡ አለ
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ (፪x)

ታናሽነቴን ፡ ያልናቀ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጠራኝ
እወድሃለሁኝ ፡ ልጄ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ አለኝ
በስደት ፡ በባርነት ፡ አገር ፡ ታሪኬን ፡ በክብር ፡ ቀየረ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ባልኩበት ፡ ጊዜ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ አብሮኝ ፡ ነበረ (፪x)

(አይቻለሁ) ፡ ወዳጅ ፡ መስሎ ፡ ስንቱ ፡ ቀርቦኝ
(አይቻለሁ) ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ሲሄድ ፡ ጥሎኝ
(አይቻለሁ) ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ስቲዘኝ
(አይቻለሁ) ፡ በድካሜ ፡ እንኳን ፡ ተሸከምከኝ

አይለወጥ ፡ ፍቅርህ
አይሰለች ፡ ትክሻህ
የሚያልፈው ፡ ሁሉ ፡ ሲጸየፈኝ
ቁስሌን ፡ ጠራርገህ ፡ አነሳኸኝ

አይለወጥ ፡ ፍቅርህ
አይሰለች ፡ ትክሻህ
የሚያልፈው ፡ ሁሉ ፡ ሲጸየፈኝ
አባት ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የተጠጋኸኝ

(አይለወጥ ፡ ፍቅርህ (፫x))
(አይሰለች ፡ ትክሻህ)

ከወንድም ፡ አብልጦ ፡ የሚጠጋጋ ፡ ወዳጄ
እኔስ ፡ አላየሁም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመች
ሁሉም ፡ በሸሸበት ፡ በዚያ ፡ በከባዱ ፡ ጊዜ
ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያወጣኝ ፡ ከሃዘን ፡ ከትካዜ (፪x)

አቤት ፡ የአንተስ ፡ ፍቅር ፡ አቤት ፡ ቸርነትህ
ለጠላትስ ፡ አይቀር ፡ በመስቀል ፡ መሞትህ
ልቤ ፡ አቅም ፡ አጣ ፡ በፍቅርህ ፡ ጉልበት
ተሸነፍኩኝ ፡ በቃ ፡ ገዛኝ ፡ ማንነትህ (፪x)

ማን ፡ ብዬ ፡ እጠራሃለሁ
ፍቅርህ ፡ ከምለው ፡ በላይ ፡ ነው
ኢየሱሴ ፡ ትለያለህ
እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ወዳጅ ፡ አለ (፪x)