ውበት ፡ እና ፡ ግርማህ (Webet Ena Germah) - ናሆም ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ናሆም ፡ ማርቆስ
(Nahom Markos)


(1)

እውነተኛ ፡ ሰላም
(Ewnetegna Selam)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የናሆም ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Nahom Markos)

አዝ፦ ውበት ፡ እና ፡ ግርማህ ፡ ያማረ
ሞገስህ ፡ እጅግ ፡ የከበረ
ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ መጣሁ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ አየሁ

አስገረመኝ ፡ አገዛዝህ
ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ ይዘህ
አያልቅም ፡ ቢነገር ፡ ስራህ
ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ

ልዩ ፡ ነህ (፫x)
ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

ከአማልክት ፡ መካከል ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው
በላይ ፡ በሰማይ ፡ በታች ፡ በምድር
አንተን ፡ የሚመስል ፡ አጣሁ

ኃያልና ፡ የተፈራህ
ሥልጣናት ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ ዘለዓለም
እጅግ ፡ የጸና ፡ ነው
ዝናህን ፡ አውርቼ ፡ አልጨርሰው

አይበቁኝምና ፡ ቃላት
ለመግለጽ ፡ የአንተን ፡ ማንነት
ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልክ
ሕይወቴን ፡ ለአንተ ፡ ላስገዛልህ (፪x)

አዝ፦ ውበት ፡ እና ፡ ግርማህ ፡ ያማረ
ሞገስህ ፡ እጅግ ፡ የከበረ
ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ መጣሁ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ አየሁ

አስገረመኝ ፡ አገዛዝህ
ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ ይዘህ
አያልቅም ፡ ቢነገር ፡ ስራህ
ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ

ልዩ ፡ ነህ (፫x)
ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

ብዙ ፡ ኃያላን ፡ የነበሩ
ታላዝ ፡ ነን ፡ ብለው ፡ የተነሱ
ዛሬ ፡ ቢፈለጉ ፡ አንዳቸውም ፡ የሉ
ሞት ፡ አሸንፏቸው ፡ ተረሱ

አንተ ፡ ግን ፡ ያለህ ፡ የነበርህ
ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
የሚስተካከልህ ፡ የሌለህ

ስለ ፡ አንተ ፡ ዘምሬ ፡ መቼ/መች ፡ ጠገብኩ (፪x)
ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ አልረካሁ (፪x)
ያንስብሃል ፡ ኢሄ ፡ አይበቃህ (፪x)
ከዚም ፡ በላይ ፡ ክብር ፡ ይብዛልህ (፪x)

አይበቃህምና ፡ ልጨምር ፡ ገና
ከልቤ ፡ ይፍለቅ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና (፬x)