From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እውነተኛ ፡ ሰላም ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
የገባኝ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ስይዝ ፡ ጌታ
ብዙ ፡ ተቅበዘበዝኩ ፡ ደህንነት ፡ ፍለጋ
በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ላገኘው ፡ አንተ ፡ ጋ
ምቾቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ነህ
እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ልቤ ፡ ያረፈብህ (፪x)
ልቤ ፡ ያረፈብህ (፬x)
(ያረፈብህ (፰x))
ወርቅ ፡ ዕንቁ ፡ ቢሞላ ፡ ላይሰጠኝ ፡ ሰላም
ዕውቀት ፡ ቢደረደር ፡ አያሳርፍም
ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ ፡ ጥያቄዋ ፡ በዝቶ
መመለስ ፡ የሚችል ፡ ከወዴት ፡ ተገኝቶ
አንተ ፡ ስትገባ ፡ ወደ ፡ ሕይወቴ
ተለዋወጠ ፡ ማንነቴ
ጥያቄ ፡ ሁሉ ፡ ተመለሰ
ሰላም ፡ ደስታ ፡ በውስጤ ፡ ፈሰሰ (፪x)
በለስ ፡ ባታበቅል ፡ ፍሬዋ ፡ ባይገኝ
ምድራዊ ፡ ነገሬ ፡ ቢጨላልምብኝ
ቢጐድል ፡ ቢሞላ ፡ እኔ ፡ አልገረምም
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ሰላሜ ፡ አይጐልም
የማዳኑን ፡ ክንድ ፡ አልብሶኛል
መጐናጸፊያን ፡ ደርቦልኛል
በአምላኬ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ
ለዘለዓለም ፡ በደስታ ፡ ኖራለሁ (፪x)
እውነተኛ ፡ ሰላም ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
የገባኝ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ስይዝ ፡ ጌታ
ብዙ ፡ ተቅበዘበዝኩ ፡ ደህንነት ፡ ፍለጋ
በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ላገኘው ፡ አንተ ፡ ጋ
ምቾቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ነህ
እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ልቤ ፡ ያረፈብህ (፪x)
ልቤ ፡ ያረፈብህ (፬x)
የሚያውቁኝ ፡ በሙሉ ፡ እጅግ ፡ ተገረሙ
እንዲህ ፡ የሚያሳርፍ ፡ "ምን ፡ አገኘ?" ፡ እያሉ
ፍፁም ፡ መረጋጋት ፡ እርፍ ፡ ማለት
የትም ፡ አይገኝም ፡ በሌለህበት
ሁሉን ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼህ
ተደላደልኩኝ ፡ አረፍኩብህ
የማይለወጥ ፡ ፍቅርህ ፡ ሲነካኝ
ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ሆነብኝ (፪x)
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ
ሰላም ፡ የሆነኝ ፡ ኢየሱስ
ማንም ፡ ከእንግዲህ ፡ ኢየሱስ
የማይለያየኝ ፡ ኢየሱስ
ቁስሌን ፡ ፈውሶ ፡ ያረገኝ ፡ ደህና
አከብረዋለው ፡ ክብሬ ፡ ነውና (፬x)
|