ሙሉቀን መለሰ (Muluken Melese)
ስለምሕረትህ ስለጥበቃህ
ስለውለታህ ጌታ ሆይ ምንስ ልክፈልህ
ከበርት ወይፈኑን ከአዝርትም ምርጡን
ከሐብት ከበረክት ከአስራት ምጽዋቱን
ነፍሰእንም ጨምረእ ሚዛን ላይ ብሰፍረው
ጌታ ለውለታህ እጅግ ያነሰ ነው
በተለምዶ ቃላት ተመስገን ልበልህ
ሌላማ ምን አለኝ ላንተ የምሰጥህ
አምላክ ሆይ ውለታህ እጅግ የበዛ ነው
ቤት አልሰራልህም ዙፋንህ ሰማይ ነው
ብር ወርቁ ያንተ ነው ምን እሰጥሃለሁ
ብቻ በአንደበቴ ተመስገን እላለሁ
እንደዳዊት ልዝለል ልዘምር ልጨፍር
አዳኝነትህን ገድልህን ልናገር
ጌታ ለውለታህ የለም የምከፍልህ
የኔ ታሪክ ድርሻ አንተን ማሞገስ ነው
ሐጥያት መስራት ትቼ ወዳንተ ብመለስ
በአለም ዙሪያ ሮጬ ወንጌልን ባዳርስ
ሰማይና ምድርን እንደ ንስር ባስስ
ጌታ ውለታህን አልችልም ልመልስ