በመጨረሻው ፡ ቀን (Bemechereshaw Qen) - ሙላቱ ፡ ዘለቀ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሙላቱ ፡ ዘለቀ
(Mulatu Zeleke)

Mulatu Zeleke 1.jpg


(1)

ለጨነቀው ፡ ደራሽ ፡ ገላጋይ
(Lecheneqew Derash Gelagay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙላቱ ፡ ዘለቀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mulatu Zeleke)

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን
ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1]
የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው
ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)

ራሳቸውንና ፡ ገንዘብን ፡ የሚወዱ
ተድላን ፡ የሚፈልጉ ፡ እውነትን ፡ የሚክዱ
በቃኝን ፡ የማያውቁ ፡ የማያመሰግኑ
ይሆናሉ ፡ ተብሏል ፡ ሳያዩ ፡ የማያምኑ
ዘመኑ ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ ያስፈራል
ኧረ ፡ ክርስቲያን ፡ ሆይ ፡ ብትነቃ ፡ ይሻላል (፪x)

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን
ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1]
የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው
ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)

ለጊዜያዊ ፡ ስልጣን ፡ ሌላውን ፡ የሚያሳድዱ
መልካምን ፡ የሚጠሉ ፡ ክፋትን ፡ የሚወዱ
ለወሬ ፡ የሚሮጡ ፡ ለሀሜት ፡ የሚቸኩሉ
የቀድሞውን ፡ ፍቅር ፡ ከውስጣቸው ፡ የጣሉ
በመንደርህ ፡ አሉ ፡ ለራስህ ፡ ጠንቀቅ ፡ በል
ዘመኑን ፡ ዋጅ ፡ እንጂ ፡ አጉል ፡ አጉል ፡ ቦታ ፡ አትዋል (፪x)

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን
ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1]
የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው
ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)

ፍቅር ፡ የሌላቸው ፡ እርቅን ፡ የማይሰሙ
ለጥቅማቸው ፡ ሲሉ ፡ ፍትሕ ፡ የሚያጣምሙ
ምህረት ፡ የማያደርጉ ፡ ድሃን ፡ የሚበድሉ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ በአፍ ፡ የሚደልሉ
ያለ ፡ ሥርዓት ፡ ጥሰው ፡ የሚሄዱትን ፡ ሁሉ
ዝም ፡ አትበል ፡ ገስጽ ፡ ይህን ፡ ይላል ፡ ቃሉ (፪x)

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን
ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1]
የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው
ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)

እኔ ፡ ከተመቸኝ ፡ ምን ፡ ቸገረኝ ፡ ባዮች
በቃሉ ፡ የማይኖሩ ፡ ሰነፍ ፡ ክርስቲያኖች
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ንዋይ ፡ የሚደለሉ ፡ ሞኞች
ለሚያምኑ ፡ እንቅፋት ፡ የሚሆኑ ፡ ዝንጉዎች

አሉ ፡ በየአገሩ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ ሽሽ
እልፍ ፡ በልና ፡ ይህን ፡ ዘመን ፡ ፈትሽ
ተላላ ፡ አትሁን ፡ ክርስቲያን ፡ ሆይ ፡ ንቃ
ከወጽመድ ፡ ልታመልጥ ፡ አንሳ ፡ የጦር ፡ ዕቃ

አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን
ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1]
የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው
ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)

  1. 1.0 1.1 1.2 1.3 1.4 ፪ ጢሞ ፫:፩ (2 Timothy 3፡1)