ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ (Bechawen Tewagto Yemiyashenef) - ሙላቱ ፡ ዘለቀ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙላቱ ፡ ዘለቀ
(Mulatu Zeleke)

Mulatu Zeleke 1.jpg


(1)

ለጨነቀው ፡ ደራሽ ፡ ገላጋይ
(Lecheneqew Derash Gelagay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙላቱ ፡ ዘለቀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mulatu Zeleke)

አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x)

የሰልፉ ፡ ባለቤት ፡ እግዚአብሔር
እንደ ፡ አህዛብ ፡ አማልክት ፡ ማይቀያየር
ባሪያዎቹን ፡ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ ያወጣል
በኃይሉ ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ያደርጋል (፪x)

አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x)

በሰው ዓይን ፡ ሲታዩ ፡ አስፈሪዎች
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ግን ፡ እጅግ ፡ ቀላለሎች
ጥላቸው ፡ ተገፏል ፡ ልባችን ፡ አይፍራ
ነገ ፡ ይሆኑልናል ፡ እንደ ፡ እንጀራ (፪x)

አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x)

ድል ለተነሳው ፡ ለጠላት ፡ ዛቻ
ለሚያስፈራራን ፡ በወሬ ፡ ብቻ
እጅ ፡ አንሰጥም ፡ ነገሩ ፡ ይገለበጣል
የእግዚአብሔር ፡ ሐሳብ ፡ ይፈጸማል (፪x)

አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x)

ሁኔታዎችን ፡ አይቶ ፡ ተስፋ ፡ መቁረጥ
ወየሁ ፡ ጠፋሁ ፡ እያሉ ፡ መደናገጥ
አይሆንም ፡ ከእንግዲህ ፡ አባት ፡ አለን
በእርሱ ፡ ከአሸናፊዎች ፡ እንበልጣለን (፪x)

አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ
ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x)

ዘጸ. 15፡3 ‹‹እግዚአብሔር ፡ ተወጊ ፡ ነው ፡ ስሙም… ›› [1]
ዘጸ. 14፡14 ‹‹እግዚአብሔር ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ይዋጋል …›› [2]

  1. ዘጸአት ፲፭ ፡ ፫ (Exodus 15:3)
  2. ዘጸአት ፲፬ ፡ ፲፬ (Exodus 14:14)