ዘመኑ ፡ ሲከፋ (Zemenu Sikefa) - መዝሙረ ፡ ደረጀ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መዝሙረ ፡ ደረጀ
(Mezmure Dereje)

Mezmure Dereje 3.jpg


(3)

ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በርታ
(Tsadeq Hoy Berta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመዝሙረ ፡ ደረጀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mezmure Dereje)

አየነው : በዓይናችን : ሲንከራተት : ሰው
መንፈስህ : ርቆት : ግራ : ሲገባው

ለካስ : አእምሮዬ : የተጠበቀው
የገዛ : መሻቴን : ስላልሰጠህኸኝ : ነው
አይ : ሰው : ያላንተ : እንዴት : ደካማ : ነው
ክፉ : እና : ደጉንም : ጨርሶ : የማይለየው (x2)


ዘመኑ : ሲከፋ : ጌታ : ፊቱን : ሲያዞር
የሰው : ልጅ : እንደ : እንሰሳ : ጉድ : ሲሆን
አቤት : ክፉንማ : ጆሮአችን : ለመደው
የማለዳ : ወሬ ፡ ቀኑማ ፡ ክፉ ፡ ነው
የምንሰማው ፡ ነገር ፡ ቀኑማ ፡ ክፉ ፡ ነው
ነውሩ ፡ ??? ፡ ሆነ ፡ ማይከለከለው
የኃጥያት ፡ ባንዲራ ፡ ሁሉም ፡ በእጁ ፡ ነው
የነውር ፡ ባንዲራ ፡ ሁሉም ፡ በደጁ ፡ ነው ፡

ያልተሰማን ፡ ሰማ ፡ ያልታየውን ፡ አየ
አቤት ፡ ዘመኑም ፡ ይከፋል ፡ አቤት ፡ ሁሉም ፡ ይለወጣል
በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ያወጣል
አቤት ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ አቤት ፡ ሰው ፡ ወዴት ፡ ይሸሻል

ለካስ : አእምሮዬ : የተጠበቀው
የገዛ : መሻቴን : ስላልሰጠኸኝ : ነው
አይ : ሰው : ያላንተ : እንዴት : ደካማ : ነው
ክፉ : እና : ደጉንም : ጨርሶ : የማይለየው (፪x)

አንድ ፡ ነገር ፡ የማውቀው ፡
የእኔ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ቅዱስ ፡ ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ጻድቅ : ነው

ክፉ : ብንሰማም : ፅድቅ : የሌለ : ቢመስልም

አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ቅዱስ : ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ንጹህ : ነው
አንድ : ነገር : የማውቀው :
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ፃድቅ : ነው

ክፉ : ብንሰማም : ፅድቅ : የሌለ : ቢመስልም

አንድ : ነገር : የማውቀው
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ቅዱስ : ነው

አንድ : ነገር : የማውቀው
የእኔ : አምላክ : ዛሬም : ንፁህ : ነው