የወንጌል ፡ አደራ (Yewongel Adera) - መዝሙረ ፡ ደረጀ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መዝሙረ ፡ ደረጀ
(Mezmure Dereje)

Mezmure Dereje 3.jpg


(3)

ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በርታ
(Tsadeq Hoy Berta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመዝሙረ ፡ ደረጀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mezmure Dereje)

ለተቀበሉት : ለዚህ : አደራ
በእምነት : ቆሙ : እስከመጨረሻ
ሐዋርያቱ : ያለፉበት : ለወንጌሉ : ነው : የተሰዉት
በአሰቃቂ : ሞት : አለፈ : ሕይወታቸው
እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው
ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ላመኑበት

እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌሉን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2)

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ
ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ
ወደ : አምላኩ : መንገድ (x2)

አለ : ምስክር : አለ : መሬቱ
ጻድቃን : ስለወንጌል : የተሰዉበት
በተራቡ : አንበሶች : እየተበሉ
የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ
በሮም : ሜዳ : ላይ : ፈስሷል : ደማቸው
እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው
ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ለአመኑበት

እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2)

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ
ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ
ወደ : አምላኩ : መንገድ

በአፄ : ዘረያዕቆብ : የተሰዉት
ለወንጌሉ : ነው : ጸንተው : የቆሙት
ከነነፍሳቸው : እየተቀበሩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ
በስደት : ዘመን : በአብዮቱ : ስያንገላቷቸው : በየእሥር : ቤቱ
ጨከኑ : ለእምነት : ለሃይማኖታቸው : ለተቀበሉት : ለአደራቸው

ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ
ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ
ወደ : አምላኩ : መንገድ

እናንተ : ቅዱሳኖች : ያቆያችሁልኝ : የወንጌል : አደራ
እንዴት : ልሸከመው : እንዴት
እንዴት : ነው :?? : (እጅግ : ይከብዳልና)x2
የነገውን : ትውልድ : በእጄ : ላይ : ይኸውና

ዛሬ : ይውረድብኝ : እናንተን : የረዳው
የእግዚአብሔር : ፀጋ(x2)