From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የእርሱ : ማንነት : አስገርሞኝ
የሚገርመው : ባህሪው : አስደንቆኝ
የቁንጅናው : መጠን : ልክ : ማጣቱ
ውበቱ : እኮ : ነው : ያመጣኝ : ቤቱ
ግርማ : ሞገሱ : አስፈሪነቱ
ገናናነቱ : አንደኛነቱ
ተወዳዳሪ : አቻ : ማጣቱ
ውበቱ : እኮ : ነው : ያመጣኝ : ቤቱ
ቢሰጠኝ : ብዬ : አልመጣልኝም
ከእጁ : የሚገኘውም : አላግዋግዋኝም
ልቤን : ሲነካው : ውበቱን : እያየሁ
እያደናነቀኝ : ክብርን : ልሰጠው (x፪)
ውበቱን : ሳየው : (እንጠባጠባለሁ)x፪
ይጠፋብኛል : (የምናገረው)x፪
አይኖቼ : በእንባ : (ይታጠባሉ)x፪
በመገረም : አይን : (ፊቱን : እያየሁ)x፪
እርሱ : የእኔ : የእኔ : ነው
እኔም : የእርሱ : የእርሱ : ነኝ (x፪)
ወዳጅነቱ : አፍቃሪነቱ
የምህረቱ : የደግነቱ
መልካምነቱ : ልክ : ማጣቱ
ውበቱ : እኮ : ነው : ያመጣኝ : ቤቱ (x፪)
ቢሰጠኝ : ብዬ : አልመጣልኝም
ከእጁ : የሚገኘውም : አላግዋግዋኝም
ልቤን : ሲነካው : ውበቱን : እያየሁ
እያደናነቀኝ : ክብርን : ልሰጠው ፡ (፪)
|