መልሰን (Melesen) - መዝሙረ ፡ ደረጀ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መዝሙረ ፡ ደረጀ
(Mezmure Dereje)

Mezmure Dereje 3.jpg


(3)

ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በርታ
(Tsadeq Hoy Berta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመዝሙረ ፡ ደረጀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mezmure Dereje)

አንተ ፡ ስትናገር ፡ (ላለመስማት ፡ ብለን)፪
እንዳንቀበለው ፡ (ምክንያት ፡ ደርድረን)፪
በሃጥያታችን ፡ መጠን ፡ (ልባችን ፡ ከፋና)፪
ለአንተ ፡ እሺ ፡ እንዳይል ፡ (አፈገፈገና)፪

አቤት ፡ መልሰን
መልሰን ፡ መልሰን
ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪)

ይገርማል ፡ እሩቅ ፡ ሄደናል
ይገርማል ፡ ደጃፍ ፡ ደርሰናል
ሳናስቀድምህ፡ ተሸንፈናል(፪)

ልባችን ፡ ተሞልቷል ፡ (በዚህች ፡ ዓለም ፡ ነገር)፪
ክፉ ፡ አስገብተናል ፡ (አንተን ፡ አስወጥተን)፪
ለጆሮ ፡ የሚጥሙ ፡ (አሉ ፡ የሚያበሉን)፪
እንደመሻተችን ፡ (የሚያስተምሩን)፪

አቤት ፡ መልሰን
መልሰን ፡ መልሰን
ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪)

ይገርማል ፡ እሩቅ ፡ ሄደናል
ይገርማል ፡ ደጃፍ ፡ ደርሰናል
ሳናስቀድምህ፡ ተሸንፈናል(፪)


የበረከት : ብቻ : ሆኗል : ስብከታችን
መስቀሉን : መሸከም : አይፈልግ : ስጋችን
መንፈስህን : ዘግተን : አስመርረነዋል
በምትናገረን : ጆሯችን : ተዘግቷል

አቤት ፡ መልሰን
መልሰን ፡ መልሰን
ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪)